Tender Detail

Tender Details

  • Company Kombolcha Customs Branch (የኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)
  • Address Ethiopia Kombolcha City, Kembolcha, Ethiopia, Phone: 0116730520
  • Website
  • Deadline05 Nov 2026, 9:50 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100(አንድ መቶ ብር)
  • Bid SecurityThe bid security amount varies by lot.
  • opening dateየጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ስድስተኛው ቀን በጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅ/ፅ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚካሄድ ሲሆን ግልፅ ጨረታው 3:50 ሰዓት ተዘግቶ 4:00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ሀራጅ ጨረታው 4:30 ሰዓት የሚጀመር ይሆናል::
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale , Car Decoration Materials , Tire And Spare Parts

በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያየ ጊዜ ውርስ የተደረጉ ተሽከርካሪ/NISSAN፣ጫማ፣ኮስሞቲክስ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ምግብ ነክ፣MOBILE PHONE COVER፣የተሽከርካሪ መለዋወጫ እና ማስቲካ በግልፅ እንዲሁም የቢንቢ ብረት ፣ የገና አባት ልብስ /santasuit እና WHEE LOODER በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል::

Kombolcha Customs Branch (የኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)


ማስታወቂያ

በጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

ጨረታ ቁጥር -12/2019 ዓ.ም

በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያየ ጊዜ ውርስ የተደረጉ ተሽከርካሪ/NISSAN፣ጫማ፣ኮስሞቲክስ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ምግብ ነክ፣MOBILE PHONE COVER፣የተሽከርካሪ መለዋወጫ እና ማስቲካ በግልፅ እንዲሁም የቢንቢ ብረት ፣ የገና አባት ልብስ /santasuit እና WHEE LOODER በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል::

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን መስፈርቶቹ፡-

  1. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር መ/ቤት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ግለሰብ መጫረት ይችላል::
  2. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር መ/ቤት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ግለሰብ መጫረት ይችላል::
  3. የዚህ አንቀፅ ተራ ቁጥር (1) ድንጋጌ ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 2 ሚሊየን በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (ሰርትፍኬት) ማቅረብ አያስፈልገውም::
  4. በጨረታ የሚሸጠው እቃ በኮሚሽኑ ቁጥጥር ስር ከመግባቱ በፊት ባለቤት የነበረ ወይም የባለቤቱ ወኪል ወይም ቤተሰብ የሆነ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም::
  5. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፤ አይነትና ብዛት የጨረታ ሰነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) እየከፈሉ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው (6) ቀን 03:00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ::
  6. ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታው የዕቃዎችን ዝርዝር በያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሀዝና በፊደል ገልፀው እና በተራ ቁጥር 1 ላይ የተገለፁትን በኤንቬሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን 3:50 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው::
  7. የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ስድስተኛው ቀን በጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅ/ፅ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚካሄድ ሲሆን ግልፅ ጨረታው 3:50 ሰዓት ተዘግቶ 4:00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ሀራጅ ጨረታው 4:30 ሰዓት የሚጀመር ይሆናል::
  8. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ05 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በመክፈል ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርባቸዋል:: በተሰጠው የጊዜገደብ ከፍለው የማይወስዱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ እቃው እንደገና ለጨረታ ይቀርባል::
  9. ተጫራቾች ለእቃዎች በሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ አሸናፊ ከሆኑ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ 15% (VAT) የሚጨመርበት ይሆናል::
  10. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን ድረስ ለሽያጭ የተዘጋጁ እቃዎችን በኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ8:00 ሰዓት እስከ 10:00 ሰዓት ድረስ እና ስድስተኛው ቀን ጧት 3:00 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ::
  11. ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ እቃዎች የሰጡትን የመግዣ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና ለሀራጅ ጨረታ የእቃው መነሻ ዋጋ ከ 2 ሚሊየን ብር በላይ ለሆነ እቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 200,000 መቶ ሺህ ብር እንዲሁም የእቃው መነሻ ዋጋ ከ 2 ሚሊየን ብር በታች ለሆነ እቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000 መቶ ሺህ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ጋር ማቅረብ አለባቸው::
  12. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 033 551 06 93 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::

ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Kombolcha Customs Branch is selling confiscated goods via open and auction tender: a Nissan vehicle, shoes, cosmetics, electronics, food items, mobile phone covers, vehicle spare parts, mastic, bingbi metal, Santa suits and a wheel loader. Bidders need a valid business licence, VAT registration, tax clearance and TIN; VAT certificate not required for items under 2 million birr.
Save Tender