የጽህፈት መሳሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃ፣ የደንብ ልብስ እና የኤሌክትሮኒክስ ግዥ - የጋርዱላ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ
በደቡብ ኢ/ክ/መንግሥት የጋርዱላ ዞን ፋይናንስ ፕላን ልማት መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢ/ክ/መንግሥት የጋርዱላ ዞን ፋይናንስና ፕ/ል/መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሴክተር መ/ቤቶች :-
- የጽህፈት መሳሪያና ለሎች አላቂ የቢሮ ዕቃ
- የደንብ ልብስ እና
- የኤሌክትሮኒክስ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ :-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፡
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /Tin No /ያላቸው፡
- የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ለደንብ ልብስ 30,000/ሰላሳ ሺህ ብር/፣ለጽህፈት መሳሪያና ለሎች አላቂ የቢሮ ዕቃ እና ለኤሌክትሮኒክስ 40,000/አርባ ሺህ ብር /በጥሬ ገንዘብ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም የባንክ ዋስትና የአገልግሎት ጊዜው 90/ዘጠና/ቀናት እና ከዚያ በላይ የሆነ ማቅረብ የሚችሉ፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከጋርዱላ ዞን ገቢዎች ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ 400/አራት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማዘጋጀት በሁለት የተለያዩ ፖስታ በማሸግ ኦርጅናሉ ላይ ኦርጅናል ኮፒው ላይ ኮፒ ብሎ በመፃፍ ፊርማና ማህተም በማድረግ በዚህ ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በ16 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ውስጥ እስከ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው፡፡ 16ኛው ቀን መደበኛ የሥራ ቀን ካልሆነ በምቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ጨረታው በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጋርዱላ ዞን ፋይናንስ ፕ/ል/መምሪያ ግዥ ክፍል ከረፋዱ 4:30 ላይ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በሰዓቱ ያለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉልም፤
- ጨረታዎቹ አሸናፊዎች ተለይተው ከተገለፀላቸው ከ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ከባድ ችግር ካልተፈጠረ በስተቀር በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አሸናፊዎች የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መግባት አለባቸው፡፡ ተሸናፊዎች ደግሞ ያስያዙትን የጨረታ ዋስ ማስከበሪያ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ያሸነፋትን ዕቃ እስከ ጋርዱላ ዞን ፋይናንስና ፕ/ል/መምሪያ መጋዘን ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፤
- መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ:- 0920978389/0941046779 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የጋርዱላ ዞን ፋይናንስና ፕ/ል/መምሪያ
✨ messages.ai_summary
Gardula Zone Finance and Plan Development Department seeks suppliers for stationery and consumable office supplies, uniforms, and electronics via open tender. Bidders need a renewed business license, commercial registration, VAT registration, TIN, supplier registration certificate, and a 90-day bid security.
