Tender Detail

Tender Details

  • Company ETHIOPIAN LOTTERY SERVICE (የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት)
  • Address ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አጠገብ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-126-78-16
  • Website
  • Deadline04 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500(አምስት መቶ ብር)
  • Bid Securityሎት-1፡ ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር)፤ ሎት-2፡ ብር 130,000.00 (አንድ መቶ ሰላሳ ሺህ ብር)
  • opening dateጥቅምት 25 ቀን 2019 ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የጽሕፈት መሳሪያና የጽዳት መገልገያ ዕቃዎችን ከአቅራቢ. ድርጅቶች በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ውድድር መሠረት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ETHIOPIAN LOTTERY SERVICE (የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት)


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ኢሎአ/004/2019

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የጽሕፈት መሳሪያና የጽዳት መገልገያ ዕቃዎችን ከአቅራቢ. ድርጅቶች በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ውድድር መሠረት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

ሎት-1፡ የጽሕፈት መሳሪያና ልዩ ልዩ አላቂ ዕቃዎች፤

ሎት-2፡ የጽዳት መገልገያ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ሁሉ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ በዚህ ሥራ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ስም በተከፈተ የባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000004652782 ገቢ በማድረግ ዋናውን ማስረጃ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ሎት-1 ላይ የሚወዳደሩ ድርጅቶች በጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ያለባቸው በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ስም ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) እንዲሁም ሎት-2 ላይ የሚወዳደሩ ድርጅቶች የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ያለባቸው ብር 130,000.00 (አንድ መቶ ሰላሳ ሺህ ብር) በሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ በማስያዝ ዋናውን ማስረጃ ከጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች በስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ውስጥ የተደራጁ ህጋዊ ጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት በጨረታው ለመወዳደር የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ያለባቸው ከአደራጃቸው ተቋም የሚያቀርቡት የድጋፍ ደብዳቤ ውስጥ መካተት ያለባቸው ሁኔታዎች የሚወዳደረበትን ተቋም ስም፣ የሚወዳደረበትን የግዥ ዓይነት፣ የጨረታ ቁጥር እና የጨረታ ማስከበሪያውን.የገንዘብ መጠን በግልጽ በአሃዝና በፊደል የተገፈ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች የቴክኒካልና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዶችን የያዘ አንድ ዋና እና አንድ ቅጂ ለየብቻው በፖስታ በማድረግና በፅሁፍ በመለየት የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ክሊራንስ፣ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት፣ የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የሚገባበት ቅፅ እና የጨረታ ማስከበሪያውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ የመጫረቻ ሰነዶቻችሁን አሚልታችሁ እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ.ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ጥቅምት 25 ቀን 2019 ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡

አገልግሎቱ ስለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-126-78-16 ደውሎ መረዳት ይቻላል፡፡

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Lottery Service seeks suppliers for stationery and miscellaneous consumables (Lot 1) and cleaning/janitorial supplies (Lot 2) via open tender. Bidders must submit technical and financial documents, renewed business license, VAT and TIN certificates, clearance, supplier registration certificate, and anti-fraud declaration.
Save Tender