Tender Detail

Tender Details

  • Company በአሪ ዞን ጂንካ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት
  • Address ጂንካ ከተማ : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-7-75-02-56
  • Website
  • Deadline05 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 300
  • Bid Securityቢሮ አላቂ እቃዎች እና ጽ/መሣሪያ ብር 30,000፤ ስፖርተኞች ምግብ ብር 15,000 (CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ)
  • opening dateበዚያው ዕለት 4:30
  • Categories Office Supplies And Services , Catering And Cafeteria Services , Stationery Materials

በአሪ ዞን ጂንካ ከተማ አስተዳደር ፋ/እና/ፐ/ጽ/ቤት ለጂ/ከ/አስተዳደር ለሴክተር መ/ቤት የቢሮ አላቂ እቃዎች የጽ/መሣሪያ እና የ1ኛ ሊግ እግር ኳስ ክለብ ስፖርተኞች ምግብ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መመገብ እና ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

በአሪ ዞን ጂንካ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በአሪ ዞን ጂንካ ከተማ አስተዳደር ፋ/እና/ፐ/ጽ/ቤት ለጂ/ከ/አስተዳደር ለሴክተር መ/ቤት የቢሮ አላቂ እቃዎች የጽ/መሣሪያ እና የ1ኛ ሊግ እግር ኳስ ክለብ ስፖርተኞች ምግብ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መመገብ እና ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው :- በዘርፉ የንግድ ፍቃድ ያላቸው ፣ የዘመኑን ግብር ከፍለው ያጠናቀቁ ፣ የንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ መሆን ይኖርባቸዋል ፡፡ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የጂ/ከ/አስ/ፋ/ጽ/ቤት የግዥ ስራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ 300 / ሶስት መቶ ብር / በመክፈል መውሰድ ይኖርባቸዋል ፡፡ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ( ቫት ) ተመዝጋቢ መሆን ይገባቸዋል ፡፡ ተጫራቾች የንግድ ፍቃድ ምስክር ወረቀት ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣ የግብር ግዴታን ስለመወጣቱ ስልጣን ካለው አካል ወይም ገቢዎች ባለስልጣን የ2019 ዓ.ም የታደሰ ከግብር እዳ ነፃ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የሰነዱን አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንቶች ኦርጅናሉን ከኦርጅናሉ ጋር ኮፒውን ከኮፒው ጋር በማድረግ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን / የቢሮ አላቂ እቃዎች እና ጽ/መሣሪያ 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/ / የስፖርተኞች ምግብ 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ኦርጅናል ዶክመንታቸውን ይዘው መቅረብ አለባቸው ። አሸናፊው ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ስራ ለመፈፀም ያሸነፉበት ገንዘብ 10 % ሲያሲዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ወይም ቀኑ በስራ ቀን ካልዋለ በማግስቱ የስራ ቀን 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት በ4:30 ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ : መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ጨረታ በሚከፍትበት ወቅት የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0467750266 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የአሪ ዞን የጂ/ከ/ፋ/ እና ፕ/ል/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Supply of office consumables and stationery, plus catering for athletes of a First League football club, for the Ginka town administration sector office. Bidders need a valid trade licence in the field, renewed for the current year, tax clearance, and VAT registration. The office may cancel the tender in whole or in part.
Save Tender