Tender Detail

Tender Details

  • Company Siinqee Bank Share Company (ሲንቄ ባንክ አ.ማ)
  • Address ኦዳ ታዎር 5ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 557 1099
  • Websitehttps://siinqeebank.com/
  • Deadline28 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price500(አምስት መቶ ብር)
  • Bid Securityየጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ ወይም 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሠነድ (CPO)
  • opening date18/02/2019 (ጥቅምት 18,2019) ዓ.ም ከረፋዱ/ከቀኑ 4:30 ሰዓት
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure , Agricultural Materials , Machinery And Vehicles

ሲንቄ ባንክ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን እና ተበዳሪዎች በገቡት ውል መሠረት ብድሩን በወቅቱ ባለመክፈላቸው ምክንያት የተረከባቸውን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::

Siinqee Bank Share Company (ሲንቄ ባንክ አ.ማ)


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 020/2019

ሲንቄ ባንክ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን እና ተበዳሪዎች በገቡት ውል መሠረት ብድሩን በወቅቱ ባለመክፈላቸው ምክንያት የተረከባቸውን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::

ተ.ቁየተበዳሪው ስምየቀድሞው የንብረቱ ባለቤትየንብረቱ ዓይነትየባለቤትነት ማረጋገጫ ሠነድ/ሠሌዳ ቁጥርየቦታው ስፋት በካሬ ሜትርንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ ከተማንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ ክ/ከተማ ቀበሌ/ወረዳየጨረታ መነሻ ዋጋ
1ኢኮ ፓይፕ ልማት ኃ/የተ/ግል ማህበርቃል ዩኒፎርምመጋዘንSUL/235/20055,000ሸገርመነአብቹ34,747,630.98
2ራሔል ሐብታሙሐብታሙ ፍሮምሳመኖሪያ ቤትWBIFL/8047/2013160ሆለታሆለታ2,305,685.87
3ደሚቱ እና ደጀኔ ኃ/የተ/የግ/ማቢኒያም ዋቆመኖሪያ ቤትB-411/4050/00160ዶዶላመልካ ዋቤ1,579,321.95
4ሰለሞን አደላ እና ታምራት ኃ/የተ/ግ/ማበርሰለሞን አደላ እና ታምራት ኃ/የተ/ግ/ማበርትራክተርOR-SM4582መልካ ሶዳሶዳ4,784,162.80

በመሆኑም:-

  1. ካዛንቺስ በሚገኘው የሲንቄ ባንክ ዋናው መ/ቤት (ኦዳ ታወር) 5ኛ (አምስተኛ) ፎቅ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ 15 % ታ.እ.ታ (VAT) ጨምሮ ብር 500 (አምስት መቶ) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ::
  2. ንብረቱን ለማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 18/02/2019 (ጥቅምት 18, 2019) ዓ.ም ድረስ ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ በአካል በመገኘት መጎብኘት ይቻላል::
  3. ተጫራቾች የንብረቶቹን የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ ወይም 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሠነድ (CPO) በሲንቄ ባንክ ስም አሰርቶ በማቅረብ መወዳደር ይችላሉ::
  4. አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ገንዘብ በ10 (አሥር) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል::ይህ ባይሆን ግን ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ የማይመለስለት ሲሆን ጨረታውን ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ አሸናፊው ከተለየ በኋላ ይመለስላቸዋል::
  5. ተጫራቾች ንብረቱን የሚገዙበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በባንኩ ዋና መ/ቤት ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል ኦዳ ታወር 5ኛ ፎቅ ላይ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 18/02/2019 (ጥቅምት 18,2019) ዓ.ም ከረፋዱ/ከቀኑ 4:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  6. ጨረታው በ 18/02/2019 (ጥቅምት 18,2019) ዓ.ም ከረፋዱ/ከቀኑ 4:30 ሰዓት በዋናው መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
  7. ሁለት ዓመት እና ከዚያ በላይ ካገለገለ መኖሪያ ቤት , ውጭ ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ታክስና ግብሮችን ገዢው/አሸናፊው ይከፍላል::
  8. ባንኩ ንብረቱን ለመሸጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው::
  9. ለበለጠ ማብራሪያ ሲንቄ ባንክ ዋና መ/ቤት በስልክ ቁጥር 0115526175 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል:
✨ messages.ai_summary
Siinqee Bank is auctioning repossessed assets—a warehouse, two residential houses, and a tractor—seized after borrowers defaulted on loans. Bidders must buy the tender document, submit a 25% CPO bid security, and pay the full winning price within 10 days; applicable taxes are the buyer's responsibility.
Save Tender