Tender Detail

Tender Details

  • Company አልትሜት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline31 Oct 2026, 12:00 PM
  • magazineReporter
  • Bid Document Price500(አምስት መቶ ብር)
  • Bid Securityከ10% (አስር በመቶ) የጨረታና ውል ማስከበሪያ C.P.O.
  • opening dateጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ/ም ፣ ጠዋት 4:30 ሰዓት
  • Categories Cargo Vehicle , Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

አልትሜት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከዚህ በታች የተገለፁትን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች አዲስ አበባ ከተማ ላይ ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::

አልትሜት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር


ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር፡ አልት/ ተሽጨ/ 01 /2019

አልትሜት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከዚህ በታች የተገለፁትን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች አዲስ አበባ ከተማ ላይ ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::

ተራ ቁጥርለጨረታ የቀረቡት ተሽከርከሪዎች ዓይነትብዛት
1ተሳቢዎች (Hi-bed and truck trailers)03በድርጅቱ ስም የተመዘገበ
2ዶዉ. የጭነት ተሽከርካሪ (DAEWOO CARGO TRUCK)02በድርጅቱ ስም የተመዘገበ
3ዶዉ. ተሳቢ ጎታች (DAEWO POWER TRUCK)01በድርጅቱ ስም የተመዘገበ
4ሞሶ ዶው ( MUSSO DAEWOO 4 seater)01በድርጅቱ ስም የተመዘገበ
5ማህንድራ ቦሌሮ ፒክ አፕ (MAHINDRA pickup)05በድርጅቱ ስም የተመዘገበ
6ዲስከቨሪ ላንድሮቨር (DISCOVERY)03በድርጅቱ ስም የተመዘገበ
7ላንድሮቨር (LANDROVER)07በድርጅቱ ስም የተመዘገበ
8ዶው ቲኮ (DAEWOO TICO)04በድርጅቱ ስም የተመዘገበ
9ዳፍ ተርቦ ከነተሳቢው (DAF TURBO with trailor)01በድርጅቱ ስም የተመዘገበ
10ሬንጅ ሮቨር (RANGE ROVER02በድርጅቱ ስም የተመዘገበ
11ቶዮታበድርጅቱ ስም የተመዘገበ
12ቢ.ኤምደብልቪ.ው (BMW)01በድርጅቱ ስም የተመዘገበ
13ዶዉ. ኖቨስ የጭነት ተሽከርካሪ (DAEWOO K8CCF NOVUS CARGO TRUCK02በግለሰብ ስም የተመዘገበ
14ተሳቢዎች (truck trailers)02በግለሰብ ስም የተመዘገበ
15ዶዉ. ተሳቢ ጎታች (DAEWO V3T8F POWER TRUCK)01በግለሰብ ስም የተመዘገበ
  1. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎች በሚከተሉት ሁለት ቦታዎች ከሰኞ -ቅዳሜ ዘወትር በስራ ሰዓት በመገኘት ማየት ይችላሉ::
    1. 1.1. ሸገር ፣ ገላን ከተማ ክፍለ ከተማ ፣ ልዩ ስሙ ሲዳ አዋሽ፣ ከአዳ ኢንተግሬትድ ትራንስፖርት ነዳጅ ማደያ አጠገብ በሚገኘው ቤዛ ኢንዱስትሪ ቅጥር ግቢ ዉስጥ
    2. 1.2. አዲስ አበባ፣ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 08፣ ስብስቴ ነጋሲ አንደኛ ደረጃ ት.ቤት አጠገብ ወይም ንፋስ ስልክ ፖሊ. ቴክኒክ ኮሌጅ ፊት ለፊት ከሚገኘው የድርጅቱ ቅጥር ግቢ ዉስጥ
  2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመክፈል ፣ አዲስ አበባ፣ ንፍስ ክፍለ ከተማ ፣ወረዳ 08 የቤት ቁጥር ቤት ቁጥር 297/8 ስብስቴ ነጋሲ አንደኛ ደረጃ ት.ቤት አጠገብ ወይም ንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ፊት ለፊት ከሚገኘው አልትሜት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ፋይናንስ ክፍል ለጨረታዉ የተዘጋጀዉን ሰነድ ከመስከረም 23 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ መግዛት ይችላሉ::
  3. ተጫራቾች አንድ እና ከዛ በላይ ተሽከርካሪ ተወዳድረዉ መግዛት ይችላሉ:: ሊገዙ የሚችሉበትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ በቀረበዉ የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ በተናጠል በመሙላት ከ10% (አስር በመቶ) የጨረታና ውል ማስከበሪያ C.P.O. ጋር እያይዘዉ በሰም በታሸገ ፖስታ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ጥቅምት 21 ቀን 2019 ዓ/ም. ከቀኑ 6:00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ፣ ንፍስ ክፍለ ከተማ ፣ወረዳ 08 የቤት ቁጥር ቤት ቁጥር 297/8፣ ስብስቴ ነጋሲ አንደኛ ደረጃ ት.ቤት አጠገብ ወይም ንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ፊት ለፊት ከሚገኘው አልትሜት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ፋይናንስ ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ::
  4. ጨረታዉ ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ/ም ፣ ጠዋት 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች/ ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ/ በተገኙበት በአልትሜት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ይከፈታል::
  5. ጨረታዉ ከመካሄዱ በፊትም ሆነ ከተካሄደ በኋላ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብት አለዉ::
  6. ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡ 0114 423077 ደዉለዉ ማግኘት ይችላሉ::

አልትሜት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር
አዲስ አበባ

✨ messages.ai_summary
Altmet PLC is selling used vehicles by open bid in Addis Ababa, as-is where-is. Vehicles include truck trailers, Daewoo cargo/power trucks, pickups, Land Rovers, Range Rovers, BMW and others. Bidders may buy one or more vehicles and must submit a 10% bid and contract guarantee CPO.
Save Tender