በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍል ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍል ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ የተለያዩ የደንብ ልብስ/ሎት አንድ/ የተለያዩ የቢሮ ጽህፈት መሳሪያ ዕቃዎች /ሎትሁለት/ የተለያዩ ህትመት ዓይነቶች /ሎት ሶስት/ የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች /ሎት አራት/፤ የተለያዩ የአይቲ ዕቃዎች /ሎት አምስት / የተለያዩ የመኪና ዕቃዎች /ሎት ስድስት/ የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎች /ሎት ሰባት/ ፤የተለያዩ የህንፃ ቁሳቁስ መገጣጠሚያ ጥገና ዕቃዎች /ሎት ስምንት/፤ መስተንግዶ /ሎት ዘጠኝ/ እና የኮምፒተር ፣ፕሪንተር ፣ፎቶ ኮፒ እና ጀኔሬተር ጥገና ባለሙያ /ሎት አስር/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።
- ተጫራቾች በዘርፍ የንግድ ሥራ የተሠማሩበት ህጋዊ የዘመኑ ግብር የከፈሉበት ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬት ያላቸው፤ ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑንን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ ክሊራንስ የሚያቀርቡ፤ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሠርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
- በአነስተኛ ጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ ከአደራጀው አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ሙሉ ቀን ጨምሮ ከጦር ኃይሎች በታች አጉስታ ድልድል በላይ ካልዲስ ኮፌ አጠገብ ባለው ነጭ ፎቅ ውስጥ በሚገኘው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት 4ኛ ፎቅ ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሠነዱን በጥሬ ገንዘብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ የቴክኒካል ሠነድ ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ኤንቨሎፕ ; እና የፋይናንሻል ዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ኤንቬሎፕ የድርጅቱ ስም ፣ አድራሻ ፣ስልክ እና ማህተም እንዲሁም የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት /ሎት/ በመፃፍ በየሎቱ በመለየት በታሸገ ኤንቬሎፕ በማቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ በመ/ቤታችን በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ ብር 5000.00/አምስትሺህብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ./C.P.O./ ወይም የባንክ ዋስትና በድ/ቤታችን ማለትም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት(Addis Ababa City Government Revenue Bureau Kolfe Keranyo Sub City Small Tax Payer Branch Office) ስም በማሰያዝ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ከ 9/2/2019 እስከ 19/2/2019 ዓ/ም 11:15 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።የሚቀርበው የመወዳደሪያ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፤ የፎቶ ኮፒ ቀለምና የፕሪንተር ቀለም የምትጫረቱ የዋስትና ደብዳቤ ማያያዝ ይኖርባችኋል።
- የጨረታ ሣጥኑ በ22/2/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድ/ቤታችን የግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ክፍል ውስጥ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ።
- አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ ዋጋ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ከዚህ በላይ ከተዘረዘሩት መስፈርቶች ውጭ በሰነዱ ላይ ባለው መመሪያ ተፈፃሚ ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ፡-በስልክቁጥር 011-369-08-56/0113836636 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Addis Ababa Kolfe Keranyo Small Taxpayers Branch Office seeks suppliers for various goods in ten lots: uniforms, stationery, printed materials, cleaning supplies, IT items, vehicle parts, fixed assets, building maintenance materials, catering, and computer/printer/photocopier/generator maintenance. Bidders need a valid trade license, supplier registration, VAT certificate, tax clearance, and TIN. Samples required.
