የጽህፈት መሳሪያ፣ ደንብ ልብስ፣ ህትመት፣ ጽዳት፣ የተሽከርካሪና የማሽነሪ ጥገና፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸርና የህክምና ዲሞንስትሬሽን እቃዎች ግዥ (10 ሎቶች) - የዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
የዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
የጨረታ ማስታወቂያ
የዳግማዊምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት የአንደኛው ዙር ግልፅ ጨረታ፣ሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሳሪያ ፣ ሎት2. ደንብ ልብስ እና የደንብ ልብስ ስፌት ፣ሎት 3 የህትመት ስራዎች፣ ሎት 4 አላቂ የጽዳት ዕቃዎች ፣ሎት 5. የተሽከርካሪ ጌጣጌጥ እና ጥገና እቃዎች ፣ሎት 6 ለፕላንት ማሽነሪ እና ለመሳሪያ እድሳትና ጥገና ፣ ሎት 7 ለቢንቢ እና ለኤሌክትሪክ ጠቅላላ ጥገና አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች ሎት 8 ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ሎት 9.ቋሚ የፈርኒቸር እቃዎች እና ሎት 10 ቋሚ የዲሞንስትሬሽን(የህክምና ) እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሟሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።
- በመስኩ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልጽ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢ የተሰጠ ማስረጃ እና የግብር መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከወሰዱት የጨረታ ሰነድ ዋጋ ዝርዝር ማቅረቢያ ውጪ በሌላ ሞልቶ ቢያቀርቡ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ጫራቾች የሚያቀርቧቸውን ዕቃዎች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ከፍለው መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል እና ፋይናንሺያሉን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው፤ በ11ኛው ቀን እስከ አራት ሰአት ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው እለት ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ የግዥ ዳርክቶሬት ቢሮ የሚከፈት ሲሆን 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
- በጨረታው ለመሳተፍ ከሎት 1 ፣2፣3፣4፣5 ፣6 እና 7 ላለው ለእያንዳንዱ ሎት 10,000.00 /አስር ሺ ብር/ ሎት 9. 20,000(ሃያ ሺ) የጨረታ ማስረከቢያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ሲኖርባቸው እና ሎት 8 እና 10. 50,000 ብር (ሃምሳ ሺ) ብር የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው ።
- ዘግይተው የቀረቡ የመወዳደሪያ ሠነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ የሚሆኑ ሲሆን ወደፊትም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ ይደረጋል።
- በጨረታው ተወዳድሮ ያሸነፈውን እቃ በኮሌጁ ጥራት /ቴክኒክ/ኮሚቴው) ጥራቱ ሲረጋገጥ ተጫራቹ በራሱ ትራንስፖርት ጭኖ በኮሌጁ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል ።
- ተጫራቾች ለጨረታው ያቀረቡት ዋጋ የሚቆይበት ጊዜ ቢያንስ ለ60 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል ።
- ኮሌጁ አሸናፊውን ተጫራች በሚመርጥበት ጊዜ የሚገዛውን እቃ ወይም አገልግሎት ብዛት /መጠን እንደአስፈላጊነቱ እስከ 20 በመቶ ለመቀነስ ወይም ለመጨመር መብት ይኖረዋል።
- የዳ/ም/ህ/ጤ/ሳ/ኮሌጅ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄ ወይም መረጃ ማግኘት ሲፈልጉ በስልክ ቁጥር 0111-26-16-53 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ :- ዳግማዊ ሚኒሊክ ኮፕሬሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው
የዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
✨ messages.ai_summary
Procurement of stationery, uniforms and tailoring, printing, cleaning supplies, vehicle parts/maintenance, plant machinery repair, electrical maintenance items, electronics, furniture and medical demonstration items, in 10 lots. Bidders must be registered suppliers with renewed business licence, tax clearance, TIN and VAT status, and submit samples where required.
