የአንድነት ፓርክ የመኪና ማቆሚያ ሕንፃ (ፓላስ ፓርኪንግ) ለቢሮ አገልግሎት ወይም ለሱቅ አገልግሎት የሚሆን ክፍሎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል፡፡
የአንድነት ፓርክ የመኪና መቆሚያ ህንጻ (ፓላስ ፓርኪንግ)
ግልጽ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ለቢሮ ወይም ለሱቅ አገልግሎት የሚውል ኪራይ የጨረታ ቁጥር 1/2019
የአንድነት ፓርክ የመኪና ማቆሚያ ሕንፃ (ፓላስ ፓርኪንግ) ለቢሮ አገልግሎት ወይም ለሱቅ አገልግሎት የሚሆን ክፍሎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡
- በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ ሞልተው የሚያቀርቡበት ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዞ በቀረበው ሰነድ ቅደም ተከተል መሠረት ቫትን ጨምሮ ነው፡፡
- ተጫራቾች የቦታውን ግምት በካሬ በተቀመጠው የመነሻ ዋጋን ተንተርሶ የሚቀርብ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሚያሸንፉበት ቦታ ላይ ለሽያጭ የሚያቀርቡትን ዕቃና አገልግሎት እንዲሁም የድርጅታቸውን ሙሉ ፕሮፋይል ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
- እያንዳንዱ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ በጽ/ቤቱ ስም ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት በጽ/ቤቱ እንግዳ መቀበያ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- እያንዳንዱ ተጫራች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- እያንዳንዱ ተጫራች ከተሰማሩበት ንግድ ሥራ ዘርፍ ውጪ በሆነ ንግድ ፍቃድ መወዳደር አይችሉም፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 ተዘግቶ በዕለቱ ከሰዓት 8:15 ሰዓት ይከፈታል ፡፡
- ፓርኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር +25111-1-54-31-03/+25118578718 ፋክስ ቁጥር 226292
የአንድነት ፓርክ የመኪና ማቆሚያ ሕንፃ (ፓላስ ፓርኪንግ)
✨ messages.ai_summary
Andinet Park (Palace Parking) is leasing office or shop units via open tender. Bidders must hold a valid, renewed trade license in the sector, provide proof of tax payment, submit technical and financial documents in separate envelopes, and bid only in their licensed sector.
