የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች (ባጃጅ ተራ፣ ጂ፣ ኤች እና አይ ፓርኪንግ) ኪራይ ጨረታ - የቂርቆስ ገበያ ማዕከል አ/ማ
የቂርቆስ የገበያ ማዕከል አክስዮን ማህበር
የጨረታ ማስታወቂያ
የቂርቆስ ገበያ ማዕከል አ.ማ. ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የመኪና ማቆሚያ ከ130 እስከ 140 መኪናዎችን የሚያስተናግዱ ቦታዎች፡-
- ባጃጅ ተራ አካባቢ መኪና ማቆሚያ
- ጂ-ፓርኪንግ
- ኤች ፓርኪንግ
- አይ ፓርኪንግ
በቀንና በማታ ተኮናትረው እንዲሰሩበት ተወዳዳሪዎችን ይጋብዛል።
ስለዚህ ለመከራየት የምትፈልጉ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላችሁ ተጫራቾች ቢሮ ቁጥር A-312 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የምትከራዩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነድ ብር 300.00 በመክፈል የጨረታ ዋጋችሁን እንድታቀርቡ እያሳሰብን ጨረታው ሕዳር 7 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።
አክሲዮኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አ.አ. ቂርቆስ ክ/ከተማ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ፊትለፊት ወረዳ 10 ቤ/ቁ A-311/313
የቂርቆስ ገበያ ማዕከል አ/ማ
✨ messages.ai_summary
Rental of car parking spaces (Bajaj Tera, G, H and I parking) accommodating 130–140 vehicles, for day and night operation. Open to bidders with a valid business license. The organization reserves the right to cancel the tender fully or partially.
Not stated in the notice: bid security. Check the original document or ask the issuer.
