Tender Detail

Tender Details

  • Company በሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ የገነት ሆቴል
  • Address አዲስ አበባ ሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ /ገነት ሆቴል/ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0939500000
  • Website
  • Deadline14 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300(ሦስት መቶ ብር)
  • Bid Securityብር 5,000.00 ( አምስት ሺህ ብር ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ለገነት ሆቴል በሚል በማሠራት
  • opening dateአሥረኛው ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ ጨረታው ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የገነት ሆቴል አስተዳደር በሆቴሉ ግቢ ውስጥ ያለውን ቦታ ለሕፃናት መጫወቻ ወይም የተለያዩ ከሆቴሉ ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ኢቨንቶች ለሚያዘጋጁ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡-

በሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ የገነት ሆቴል


የቦታ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የገነት ሆቴል አስተዳደር በሆቴሉ ግቢ ውስጥ ያለውን ቦታ ለሕፃናት መጫወቻ ወይም የተለያዩ ከሆቴሉ ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ኢቨንቶች ለሚያዘጋጁ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡-

በመሆኑም

  • የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፤
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት (VAT) ያላቸው፤
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ያለው

ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን፡-

  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 ( አምስት ሺህ ብር ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ለገነት ሆቴል በሚል በማሠራት ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ለብቻው በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 10 (አሥር) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከድርጅታችን አስተዳደር ክፍል የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች ቦታውን በአካል ተገኝተው በማየት 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ እና 10% የአገልግሎት ክፍያን ጨምሮ በጥቅል ቦታውን በወር የሚከራዩበትን ዋጋ በመግለጽ ቴክኒካል መስፈርቱንና ፋይናንሱን ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ገነት ሆቴል አስተዳደር ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን እስከ አሥረኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ አስተዳደር ክፍል ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፤ አሥረኛው ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ ጨረታው ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
  • አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፡፡
  • ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ 0939-50-00-00

በሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሠልጠኛ ኢኒስቲትዩት የገነት ሆቴል

✨ messages.ai_summary
Gebeta Hotel seeks to rent out space in its compound for a children's playground or hotel-related events. Eligible bidders must have a renewed business license, VAT registration and a TIN. Bidders must inspect the site and submit technical and financial offers separately.
Save Tender