ደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ፣ የትምህርትና የፅዳት ዕቃዎች እና ልዩ ልዩ መሣሪያዎች ግዥ (5 ሎቶች, 001/2019) - አቃቂ መንግሥት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አቃቂ መንግስት የመ/ደ/ት/ቤት
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አቃቂ መንግሥት የመጀ/ደረጃ ት/ቤት በ2019 ዓ.ም የሥራ ዘመን የተለያዩ ዕቃዎችን በ1ኛ ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ፡-
| ሎት | የዕቃው አይነት | የጨረታ ማስከበሪያ (ብር) |
| ሎት 1 | ደንብ ልብስ | 23,000.00 |
| ሎት 2 | አላቂ የቢሮ ዕቃዎች | 5,000.00 |
| ሎት 3 | አላቂ የትም/ዕቃዎች | 15,001.00 |
| ሎት 4 | አላቂ የፅዳት ዕቃዎች | 5,014.00 |
| ሎት 5 | ልዩ ልዩ መሣሪያዎች | 1,851.00 |
የጨረታ ማስከበሪያ የግድ CPO ማሠራት አለበት፡፡ ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አይቻልም፡፡
- የጨረታ ቁጥር 01/2019 ዓ.ም ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ላቅርቦቱ አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ሰርተፍኬት እና የታክስ ከፋይነት ቲን ነምበር ሊኖራቸው ይገባል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 ብር በመክፈል በእያንዳንዱ ሎት CPO በማስያዝ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት 2፡30 ሰዓት እስከ 11፡30 ከግዥ ቢሮ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
- አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ሌላው ተንተርሶ መስጠት አይቻልም፡፡
- ተቋሙ ለሚገዛው ግዥ 20% ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል፡፡
- ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውን(ፋይናንሻል) እና ፎቶ ኮፒውን (ቴክኒካል) ሰነዶችን ለየብቻ በታሸገ ፖስታ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮው ለዚህ ጨረታ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት 2፡30–11፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የሚቀርበው የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ የድርጅቱ ኃላፊ ስምና ፊርማ እንዲሁም አድራሻ እና ስልክ ቁጥር መኖር አለበት፡፡
- አሸናፊ ተጫራች በሰነዱ ውስጥ በተመለከተው ጊዜ ገደብ ውስጥ ማለትም እስከ 7 ቀን ድረስ ቀርበው የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% CPO አስይዘው ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ካመነበት ከጨረታ አሸናፊ ድርጅት ጋር እስከ ስድስት ወር ድረስ ውሉን ቢያድስም ባያድስም የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ግልፅ ያልሆኑ ጉዳዮች ካሉ የማብራሪያ ጥያቄ በፅሑፍ ከጨረታው መከፈቻ ሁለት ወይም ሦስት ቀናት በፊት ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የግዥውን ውል ከፈረመበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ዕቃውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታውን አካሄድ ለማዛባትም ሆነ ለማጭበርበር የሚሞክር ማንኛውም ተጫራች ከጨረታው ውጪ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለሚያስገባቸው ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የተጫረቱበትን ዕቃዎች ናሙና ወይም ሳምፕል ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም ተጫራቾች በምታቀርቡት ናሙና/ሳምፕል/ ላይ ምንም ዓይነት ስልክ ቁጥር እና ሌሎች ምልክቶች ማድረግ ከውድድር ውጪ ያደርጋል፡፡
- ከጥቃቅንና አነስተኛ ወይም ካደራጃቸው መሥሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ይዘው የሚጫረቱ ተጫራቾች ከሆኑ ምን አይነት ምርት እንደሚያመርቱ እና የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሀገር ውስጥ ምርት ቸርቻሪ /ጅምላ ንግድ/ ከሆነ ደግሞ ከአምራቹ የተሰጣቸውን ፈቃድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ካልሆነ ግን እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ በመግዛትና የጨረታ ማስከበሪያ እና የውል ማስከበሪያ በማስያዝ መወዳደር ይችላሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011-471-56-50 ይደውሉ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የአቃቂ መንግሥት የመጀ/ደረጃ ት/ቤት
✨ messages.ai_summary
Akaki Government Primary School invites bids for five lots: uniforms, consumable office supplies, educational materials, cleaning supplies, and miscellaneous equipment. Bidders need a valid business license, tax payment proof, VAT certificate, and TIN. Samples are required.
