በድጋሚ፡ የጽህፈት፣ ጽዳት፣ ICT፣ ደንብ ልብስ፣ ህትመት፣ ኤሌክትሪክ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የተጠርጣሪ ቀለብና የተሽከርካሪ ጎማ ግዥ (14 ሎቶች, NCB 001/2019) - የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር A.K.K.K.P.D./NCB 001/2019 ዓ/ም
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት ለመምሪያው የስራ ክፍሎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ጨረታዎችን በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ሲሆን፡-
| ሎት | የጨረታ ዓይነት | የናሙና መለያ | የጨረታ ማስከበሪያ ብር |
| 1 | የጽህፈት መሳሪያዎች | ናሙና የሚቀርብባቸው | 75,000.00 |
| 2 | የጽዳትና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች | ናሙና የሚቀርብባቸው | 18,100.00 |
| 3 | የአይ ሲ ቲ (ICT) መለዋወጫ ዕቃዎች | ናሙና የሚቀርብባቸው | 26,600.00 |
| 4 | የተለያዩ ደንብ አልባሳቶች ግዥ | ናሙና የሚቀርብባቸው | 50,500.00 |
| 5 | የህትመት ውጤቶች | ናሙና የሚቀርብባቸው | 35,000.00 |
| 6 | የኤሌክትሪክና የቧንቧ መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ | ናሙና የሚቀርብባቸው | 25,900.00 |
| 7 | የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ ጥገናና እድሳት የዕጅ ዋጋ አገልግሎት | ናሙና የሚቀርብባቸው | 7,000.00 |
| 8 | የታሸገ ውሃ | 25,000.00 | |
| 9 | የተጠርጣሪ ቀለብ አቅርቦት ግዥ | ናሙና የሚቀርብባቸው | 20,000.00 |
| 10 | የመጸዳጃ ቤት ፈሳሽ ማስመጠጥ አገልግሎት | ናሙና የሚቀርብባቸው | 10,000.00 |
| 11 | የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች | ናሙና የሚቀርብባቸው | 33,000.00 |
| 12 | የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎች ግዥ፤ | ድጋፊ ሰነድና ሊብሬ | 56,000.00 |
| 13 | የተሽከርካሪዎች ጎማ፣ወንበር ልብስ፤የዝናብና ፀሐይ መከላከያ ሸራ ከነመወጠሪያው ብረት እና የመኪና ሰርቪስ ዕቃዎች ግዥ | - | 75,000.00 |
| 14 | የተሽከርካሪዎች ጎማዎች ጥገናና ዕድሳት (ጎሚስታ) | - | 2,000.00 |
| ድምር ብር | 459,100.00 |
ስለዚህ፡- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው
- የታደሰ ምዝገባ ፈቃድና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን እና በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው ይመልከቱ የሚል ፅሁፍ በግልፅ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ የያዘ(TIN) ሠርተፍኬት፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የዌብ ሣይት የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡
- ጥቃቅንና አነስተኛ በሚያመርቱት ምርት ብቻ ልዩ አስተያየት ይደረጋል፡፡
- አማራጭ ዋጋ እና አማራጭ ዕቃ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ተብሎ በተዘጋጀው ከባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ ውጤቱ አሸናፊ መሆናቸውን ከታወቀ ከ8ኛ ቀን ጀምሮ 10% የውል ማስከበሪያ ዋስትና ለአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ተብሎ በተዘጋጀው ከባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝና ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውንም ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችንና የዋጋ ማቅረቢያዎችን /ፋይናንሻል/ ሰነዶች በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ እና የሚያስገባው ሰነድ ፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የጨረታ ሰነዱን ቁጥር የሚጫረትበትን ዕቃ አይነት በትክክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታውና በዝርዝሩ ሙሉ የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማውና ማህተም በመምታት ማስገባት ያለበት ሲሆን፤ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያሲዙት ሲ.ፒ.ኦ. ከቴክኒክ ሰነዶች ጋር በአንድ ላይ ታሽገው መቅረብ አለባቸው፡፡
- በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን ወይም አገልግሎቱን በራሳቸው ትራንስፖርት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ግምጃ ቤት ወይም በክፍል 6 በፍላጎት መግለጫው በተጠቀሰው የማስረከቢያ ቦታ ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው፡፡
- በጨረታ ሰነድ በክፍል 6 ውስጥ በሚገኘው የፍላጎት መግለጫ ላይ በሚገለፀው መሰረት ጨረታ ሰነዱ ላይ በቀረበው መሰረት ናሙና ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ያቀረቡት ናሙናም ሆነ አሸናፊ መሆናቸው ሲረጋገጥ የሚያቀርቡአቸው ዕቃዎች ፖሊስ መምሪያው ባወጣው ፍላጎት መግለጫ /sepecification/ መሰረት መሆኑን በዋና መምሪያው የጥራት ኮሚቴ ወይም በኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ኤጀንሲ አማካኝነት የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡
- ናሙናው ገቢ መሆን ያለበት ጨረታው ከሚከፈትበት ከአንድ ቀን በፊት መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ጎጃም በረንዳ አሰፋው ወሰን ሆቴል ጎን በሚገኘው መ/ቤት 5ኛ ፎቅ ግዢ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ቀርበው በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ እንዲሁም በማግስቱ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ድረስ ክፍት ይሆንና በዛው ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ 5ኛ ፎቅ ኮሪደር ላይ በይፋ ይከፈታል፡፡
- ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ እንዲሁም በማግስቱ በ11ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ጨረታው ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው ዕለት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾችና የሚመለከታቸው አካላት ባሉበት በመ/ቤቱ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስ/ቁጥር 0112-73-34-04 ወይም 0112-73-37-35 ይደውሉ
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ
✨ messages.ai_summary
Addis Ketema Sub-City Police Main Department seeks suppliers for 14 lots of office supplies, cleaning materials, ICT and electronics, uniforms, printing, electrical items, suspect handcuffs, vehicle tires and related services. Bidders need renewed trade license, TIN, VAT registration, supplier website registration, and samples. Alternative prices/items not allowed.
