የህክምና መገልገያዎች፣ የላብራቶሪ ሬጀንቶች፣ የጽዳትና የጽህፈት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ደንብ ልብስና የቢሮ ፈርኒቸር ግዥ - የቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል
የቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2019 ዓ.ም በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችና መለዋወጫ፣ የላብራቶሪ ሬጀንቶች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ደንብ ልብስ OR፣የቢሮ ዕቃ/ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት የጨረታ መስፈርቱን የሚያሟሉ፤
- ለአከፋፋይነት/ለችርቻሮ የዘመኑን ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- TIN Number ያለውና VAT ተመዝጋቢ የሆነ፤
- ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/CPO/ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው፤
- ናሙናዎችን እስከ ጨረታው ድረስ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ካቀረበው ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ሁሌንም ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል ግ/ክ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 40 መግዛት ይቻላል፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- ጨረታው ይኼ ማስታወቂያ ከወጣበት ጀምሮ ለ15 ስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ፡፡ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ተዘግቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል ግ/ክ/የስራ ሂደት በሬ ይከፈታል። ዕለቱ በዓል /ዝ/ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፤
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል
✨ messages.ai_summary
Tepi General Hospital seeks suppliers for medical supplies and equipment, laboratory reagents, cleaning materials, stationery, electronics, uniforms, and office furniture via open tender. Bidders need a valid trade license, TIN, VAT registration, supplier registration certificate, and must submit samples.
