Tender Detail

Tender Details

  • Company በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ
  • Address በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ ከራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል አለፍ ብሎ ታደሰ ቸኮል ኮሜርሻል 100 ሜትር ገባ ብሎ ወረዳ 2 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251111265333
  • Website
  • Deadline27 Oct 2026, 9:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 150 (የማይመለስ)
  • Bid Securityበተወዳደሩበት ሎት 2% (CPO)
  • opening dateበዚሁ ቀን 3፡30 ሰዓት
  • Categories Textile, Garment & Leather , Medical Equipment And Supplies , Stationery Materials

ቋሚ እቃዎች፣ መድኃኒቶች፣ የላብራቶሪ ሬጀንቶች፣ የጽዳት፣ የጽህፈት፣ የደንብ ልብስ እቃዎችና የተለያዩ አገልግሎቶች ግዥ (3 ሎቶች, ስ/ከ/ጤ/ጣ/01/2019) - አራዳ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ማስታወቂያ ቁጥር ስ/ከ/ጤ/ጣ/01/2019

በአራዳ/ክ/ከ/ወ/2 የስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ በ2019 የበጀት ዓመት በሎት ከፋፍሎ ለማጫረት ይፈልጋል፡፡

  • ሎት 1 የተለያዩ ቋሚ እቃዎች፣ መዳኒቶችና የላብራቶሪ ሬጀንቶች
  • ሎት 2 የተለያዩ የጽዳት እቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብስ ጨርቆችና ጫማዎች ፣ ህንጻ፣ ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች እድሳት እና ጥገና ግብዓት እቃዎች፣ ህትመቶች፣ የመኪና ጐማና መለዋወጫ
  • ሎት 3 የውሃ ታንከር ፅዳት አገልግሎት፣ የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት የሚሰጡ፣ የጭነት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከሪካሪዎች፣ የጀነሬተር ጥገና አገልግሎት የሚሰጡ፣ የአይቲ ጥገና አገልግሎት የሚሰጡ፣ የለስላሣ አቅርቦትና መስተንግዶ አገልግሎት የሚሰጡ

በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ፡-

  1. ከሚገዛው ዕቃ /አገልግሎት/ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/Tin No/ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚገልፅ የምዝገባ የምስክር ወረቀት /በዌብሳይት የተመዘገቡ ተጫራቾች ከዊብሳይቱ ላይ ፕሪንት አድርገው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በየዘርፉ የተወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ከ50 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በተወዳደሩበት ሎት ላይ የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ 2% ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) በባንክ በተረጋገጠ በጤና ጣቢያው ስም ማቅረብ የሚገባቸው ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል፡፡
  5. ተቋማችን የሚገዛቸውን የአገልግሎት/ የዕቃዎች አይነት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በየሎቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 150 በመክፈል በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ ለዚሁ አገልግሎት ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ ግዥ ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ቫትን ያላካተተ፣ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም አድርጎ የማያቀርብ፣ ስርዝ ድልዝ ያደረገ እና አማራጭ ጨረታ የተጠቀመ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  8. የጨረታው ሣጥን በአስራ አንደኛው ቀን 3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ አዳራሽ ጨረታው በግልጽ ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የደንብ ልብሶች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ህንጻ፣ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች እድሳት እና ጥገና ግብዓት እቃዎች ጥራት ለመለየት የሚያስችል ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ ግዥ ቢሮ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡ ናሙና ያላቀረበ ተወዳዳሪ/ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  10. በቋሚ እቃዎች ላይ የሚጫረቱ ተጫራቾች ከሰነዳቸው ጋር የፎቶና እስፔስፊኬሽን ማቅረብ አለባቸው ፎቶ እስፔስፊኬሽን ያላቀረበ ተወዳዳሪ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  11. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን እቃ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ጤና ጣቢያው እቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  12. መ/ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ 20% /ሀያ ከመቶ/ጨምሮ ወይም ቀንሶ መግዛት ይችላል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡ በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ ከራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል አለፍ ብሎ ታደሰ ቾኮል ኮሜርሻል 100 ሜትር ገባ ብሎ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ +251 11 126 53 33/ 09 11 44 12 57 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ

✨ messages.ai_summary
Supply of various fixed assets, medicines, laboratory reagents, cleaning and stationery materials, uniforms, and related services, divided into three lots. Bidders must hold a valid business license and TIN, be registered on the suppliers list, and submit samples and photos with specifications.
Save Tender