አልባሳት፣ የፅሕፈት፣ የፅዳትና የግንባታ ዕቃዎች ግዥ (4 ሎቶች, ግ/ጨ/001/2019) - የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ብላቴ
የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ብላቴ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ማሠልጠኛ ማዕከል ግ/ጨ/001/2019
በሀገር መከላከያ ሚ/ር በልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠ/መምሪያ የብላቴ የልዩ ዘመቻዎች ማ/ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የትምህርት መርጃ ዕቃዎች፣የግንባታ ዕቃዎችን አላቂ የፅህፈት እና የፅዳት ዕቃዎች እንዲሁም የተለያዩ አልባሳት እና ጨርቃ ጨርቅ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም በተጨማሪ ዕሴት ታክስ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃና የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚከናወነው በግልፅ ጨረታ ስነ-ሥርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ የኢፌዴሪ መንግስት ባወጣው የመንግስት ግዥ አዋጅ ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች ነው።
- አሸናፊ ድርጅት ባሸነፋቸው እቃዎች ያሸነፉበትን ዋጋ ከጨረታው በኋላ ሳይጨምር ወይም ሳይቀንስ እስከ 90 ቀናት ማየት ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋ ሲያቀርቡ የእቃውን ሙሉ ሥም የተሰራበትን ሀገርና የጥራት ደረጃውን /Specification/ በመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ መግለፅ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በር፡-
- ለሎት 1 አልባሳት ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/
- ለሎት 2 የፅሕፈት ዕቃዎች ብር 35,000 /ሰላሳ አምስት ሺህ ብር/
- ለሎት 3 የፅዳት ዕቃዎች ብር 150,000.00/ አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ብር/
- ለሎት 4 የግንባታ ዕቃዎች ብር 50,000/ ሀምሳ ሽህ ብር/
- የጨረታው ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ብላቴ የልዩ ዘመቻዎች ማሰልጠኛ ማዕከል የግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 23 ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር ከፍለው መግዛት ይችላሉ።
- በጨረታ ሳጥን ውስጥ የመጫረቻ ሰነድ የሚገባው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ እስከ 4፡00 ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በልዩ ዘመቻዎች ማሰልጠኛ ማዕከል ቢሮ ውስጥ በሚገኘው ሚኒ መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚከፈት ሲሆን ጨረታዉ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ 4፡10 ይከፈታል።
- 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
- አሸናፊ ድርጅት ዕቃውን የማጓጓዝ ትራንስፖርት ወጪ በራሱ በመሸፈን ከሀዋሳ በስተ ደቡብ 90 ኪሎ.ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ግምጃ ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይጠበቅበታል።
- ማሠልጠኛ ማዕከሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ
ስልክ 0462280033 /0462280001/2 /0924332931 ይደውሉ!
በሀገር መከላከያ ሚ/ር በልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠ/መምሪያ የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ማሠልጠኛ ማዕከል
✨ messages.ai_summary
Procurement of educational materials, construction items, consumable stationery and cleaning supplies, plus various clothing and textiles, in 4 lots for the Bliate Special Operations Training Center. Bidders need a valid trade license, tax payment proof, VAT registration, and supplier registration certificate.
