የካፌቴሪያ አገልግሎት ሠራተኞች የአልባሳት አቅርቦት (SSNT-T650) - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
የካፌቴሪያ አገልግሎት ሠራተኞች የአልባሳት አቅርቦት ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር SSNT-T650
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የካፌቴሪያ አገልግሎት ሠራተኞች አልባሳት አምራች ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አምራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ:
- ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች እና በሙያ ዘርፉ አምስት (5) ዓመት እና ከዚያ በላይ የሰሩ ፣ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 200.00 ብር/ ሁለት መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T650 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy)፣ የጨረታውን ቁጥርና አይነት እንዲሁም የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ሃምሳ ሺህ ብር (50,000.00) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ለ150 ቀናት የሚቆይ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ተጫራቾችን የጨረታ ማስከበሪያ ለተጨማሪ ቀን የሚቆይበት ጊዜ እንዲራዘምለት የመጠየቅ መብት አለው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ቅጂውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በተለያየ ኢንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል ዓርብ፣ ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ከሰዓት 8፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን 9፡00 በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት በጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
በስልክ ቁጥር፡ +251-115-17-8025 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
ኢሜል፡ Woldem@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
✨ messages.ai_summary
Ethiopian Airlines Group seeks manufacturers to supply clothing for cafeteria service staff under contract. Eligible bidders must be qualified manufacturers with 5+ years in the field, a valid renewed business license, VAT registration, tax clearance, and a valid government tender permit.
