የ2019 ዓመታዊ የጽህፈት መሳሪያ እና የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ - በወላይታ ዞን የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት
በወላይታ ዞን የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ የፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በ2019 የበጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ የሚፈፀም ዓመታዊ መስተንግዶ እና ጽ/መሳሪያ ግዥ በደ/ኢ/ክ/መ በወላይታ ዞን የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ፋ/ፕ/ጽ/ቤት በኩል የሚከናወን ጨረታ ነው፡፡
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የሥራ ንግድ ፈቃድ ያሳደሱ ፣ የቫትና የቲን ተመዝጋቢዎች ሲሆኑ ግዥ በምንፈጽመው በዕቃ ዓይነቶች የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ/ብር በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ገ/ቅ/ጽ/ቤት በመክፈል ሠነዱን ከቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ግዥ ፋ/ን/አስ/ር ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 20 በሥራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ20ኛው ቀን ከቀኑ በ5፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ልክ በ5፡30 ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡ 20ኛው ቀን በዓል ወይም ሰንበት ከሆነ በማግስቱ በተባለው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- በግዥ ፈጻሚ መ/ቤት በኩል በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ካለ ጉዳዩን አስመልክቶ ለቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ጥያቄው በጽሑፍ ሲቀርብ ማብራሪያ ይሰጣል ፡፡
- የመጫረቻ ሀሳብ በመ/ቤታችን በኩል ተዘጋጅቶ በሚቀርብ መደበኛ የጨረታ ሠነድ እንጂ በሌላ መንገድ/ዓለማ በተዘጋጀ ሰነድ የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን ማቅረብ አይፈቀድም ፡፡
- ጨረታው የሚስተናገድበት ቋንቋ የሀገሪቱ የሥራ ቋንቋ በሆነው አማርኛ ቋንቋ ይስተናገዳል፡፡
- የጨረታ ግምገማ በጋዜጣ በተገለጸው መሠረት የጨረታ ማወዳደሪያ ዘዴው በጥቅል ዝቅተኛ ዋጋን መሠረት በማድረግ የሚፈፀም በመሆኑ በእያንዳንዱ የጽ/መሳሪያ እና የመስተንግዶ ዓይነት ዋጋ መመዝገብ ይጠበቅበታል ፡፡
- ከጨረታው ጋር በተያያዘ ሂደቱን ለማዛባት የሚፈፀሙ ማንኛውም ዓይነት ህገ-ወጥ ድርጊቶች በህግ ከማስጠየቁ ሌላ ከተወዳዳሪነት ውጭ ያደርጋል፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጡ ዕቃ ግዥ ከተፈፀመ በኋላ ለመንግሥትና ለህዝብ በትክክል አገልግሎት የሚሰጡ ጥራት ያላቸውና ጥራታቸው የተረጋገጠ ስለመሆኑ በውሉ ውስጥ ይካተታል፡፡
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሠነድ ተቀባይነት አይኖረውም ፡፡
- በዋጋ አቅርቦት ወቅት ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ተወዳዳሪዎች እኩል ዋጋ ያቀረቡ ከሆነ አሸናፊውን ተጫራች ለመለየት ሌላ የማወዳደሪያ ሀሳብ እንዲያቀርቡ/በዕጣ የመለየት የተጫራቾቹ ስምምነት ተጠይቆ ተፈጻሚ ይደረጋል፡፡
- የጽ/መሳሪያ እና የመስተንግዶ ጨረታ ዋጋ ጨረታው ይፋ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ ለአንድ ዓመት ተከታታይ ፀንቶ ይቆያል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 10000 /አስር ሺህ ብር/ጽ/መሳሪያ 25000/ሃያ አምስት ሺህ ብር/ለመስተንግዶ በባንክ የተረጋገጠ CPO፣ በጥሬ ገንዘብ እና ሴቲር እፍ ከሬዲት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ የግዥው 10% በባንክ የተረጋገጠ CPO ፣በጥሬ ገንዘብ እና ሴቲር እፍ ክሬዲት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታውን አስፈላጊ ሠነዶች የያዘ ፖስታ ዋናና ኮፒ በታሸገ ኤንቬሎፕ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ለመጫረት የሚያቀርቡት ማንኛውም ዓይነት ሠነዶች ህጋዊ ሥልጣን ባለው አካል የተፈረመ ማህተም ያረፈባቸውና ለውድድሩ አስፈላጊ ናቸው የተባሉ ሰዶች በሙሉ ህጋዊነታቸው የተረጋገጠ መሆን አለበት ፡፡
- በጨረታው ሂደት ላይ ቅሬታ ካለዎት በግዥ አዋጅ ምዕራፍ 14 አንቀጽ 44 እና 46 መሠረት አቤቱታ ማቅረብ ይቻላል ፡፡
- የጽ/መሳሪያ ናሙና ተጫራቾች የሚያቀርቡት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካለው ጨረታውን እንደአስፈላጊነቱ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0910503789 ፣ 0916684480 ወይም 0910464702 ይጠቀሙ
በወላይታ ዞን የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ የፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Annual procurement of stationery and catering services for the Boloso Sore Woreda Finance and Plan Office in Wolaita Zone. Open to eligible suppliers registered for VAT, TIN, and the relevant supplier category. Bidders must submit samples of stationery items.
