Tender Detail

Tender Details

  • Company ሬይንቦ ኤክስክሉሲቭ የመኪና ኪራይና አስጎብኚ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
  • Address , Phone: 011 371 79 44
  • Website
  • Deadline28 Oct 2026, 1:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 500 (የማይመለስ)
  • Bid Securityየመኪናው መነሻ ዋጋ 10% (ሲ.ፒ.ኦ)
  • opening dateጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ 7፡00 ሰዓት
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የጨረታ ሽያጭ (001) - ሬይንቦ ኤክስክሉሲቭ የመኪና ኪራይና አስጎብኚ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር

ሬይንቦ ኤክስክሉሲቭ የመኪና ኪራይና አስጎብኚ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር


ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001

ሬይንቦ ኤክስክሉሲቭ የመኪና ኪራይና አስጎብኚ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ከዚህ በፊት ይጠቀምባቸው የነበሩ አሥራ ስባት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይልጋል፡፡

የጨረታው መመሪያዎች፡-

  1. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከድርጅቱ በመግዛት በባንክ አካውንት ቁጥር በዳሸን ባንክ 0122001545005 ወይም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000317295484 የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ገቢ አድርገው ደረሰኙን በማቅረብ ሣር ቤት አዳምስ ፓቪሎን ወደ ቁራ በሚወስደው መንገድ ኪያብ ሕንፃ 5ኛ ፎቅ መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተሽከርካሪዎቹን ሰሚት ፋርማኪዩር ግቢ ውስጥ በአካል ቀርበው መመልከት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚፈልጉትን የመኪና አይነትና የሠሌዳ ቁጥር ከሚገዙበት ዋጋ ጋር በመጥቀስ እና ለጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የሚፈልጉትን መኪና መነሻ ዋጋ 10% (አሥር በመቶ) በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በማያያዝ ከሰኞ እስከ አርብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 5፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ሊገዙ የሚፈልጉትን ተሽከርካሪ የሚያቀርቡትን ዋጋ በተዘጋጀው የመጫረቻ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በግልጽና በማያሻማ ሁኔታ በመሙላት በሰም በታሸገ ፖስታ በማስገባት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ማግስት ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በዋናው መ/ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT) ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡
  6. አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው ነገር ግን አንድ ተጫራች ለእያንዳንዱ መኪና የጨረታ ማስከበሪያ የተጠየቀውን ሲ.ፒ.ኦ በማቅረብ ከአንድ መኪና በላይ መጫረት ይችላል፡፡
  7. ጨረታው ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በ7፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰሚት ፋርማኪዩር ግቢ ውስጥ ይከፈታል፡፡
  8. በጨረታው ለሚሸነፉ ተወዳዳሪዎች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ይመለስላቸዋል፡፡ ለአሸናፊዎች ግን ከግዢው ክፍያ ላይ ታሳቢ ይሆናል፡፡
  9. ድርጅቱ መኪናዎቹን ለመሸጥ የሚያስፈልጉ ክሊራንስ በራሱ ወጪ ከሚመለከተው መንግስት መ/ቤት ያቀርባል፡፡
  10. የጨረታ አሸናፊዎች የስም ማዛወሪያና በሽያጩ ምክንያት የሚጣለውን ማናቸውንም ግብር፣ ቀረጥና የተሽከርካሪው የሽያጭ ግምት ክፍያ እንዲሁም ለሚገዟቸው መኪናዎች ማናቸውንም ተዛማጅ አገልግሎቶች ወጪ ሙሉ በሙሉ በራሳቸው ይሸፍናሉ፡፡
  11. የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉበትን የመኪና ዋጋ ከፍለው በሰባት (7) የሥራ ቀናት ውስጥ መኪናዎቹን ማንሳት አለባቸው፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ያስያዙት ገንዘብ /ሲ.ፒ.ኦ/ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ከጨረታው አሸናፊነት ይሰረዛሉ፡፡
  12. የጨረታ አሸናፊዎች በሦስት ወራት ውስጥ የባለቤትነት ስም ዝውውር መጨረስ አለባቸው፡፡
  13. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-
አድራሻችን፡- ሣር ቤት አዳምስ ፓቪሎን ዝቅ ብሎ ወደ ቁራ በሚወስደው መንገድ በኪያብ ሕንፃ 5ኛ ፎቅ ወይም
በስልክ ቁጥር፡- 011 372 26 38 ወይም 011 371 79 44 ወይም 011 372 26 40
ኢ-ሜይል Info@rainbowethiopiatours.com አዲስ አበባ

ሬይንቦ ኤክስክሉሲቭ የመኪና ኪራይና አስጎብኚ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር

✨ messages.ai_summary
Rainbow Exclusive car rental and tour service invites bids for the sale of seventeen used vehicles, sold as-is. Bidders must buy the tender document, submit a CPO for 10% of the vehicle's starting price per vehicle, and may bid on more than one vehicle.
Save Tender