የተወረሱ ሞተር ሳይክሎች፣ መለዋወጫዎች፣ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስና ሌሎች ዕቃዎች የግልጽና የሃራጅ ሽያጭ (06/2019) - የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
ማስታወቂያ ቁጥር 06/2019
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ/ጣቢያዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ የሞተር ሳይክሎች እና የተሽከሪካሪ መለዋወጫዎች፣ አልባሳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የመገናኛ መሳሪያዎች፣ ኮስሞቲክስ እና የንጽሕና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ የቤት ውስጥ መገልገያ እና ማስዋቢያ ዕቃዎች፣ ነዳጅ፣ ምግብ ነክ ዕቃዎች፣ የጥራጥሬ እህሎች እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎች በግልጽ እና በሃራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች ማማሏት የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃዎች ጋር ተዛማችነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና መለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የግልጽ እና ሃርጅ ጨረታ ሰነድ በቴሌግራም አካውንት የሚላክላችሁ ሲሆን ተጫራቹ ለመግዛት የሚፈልገውን የዕቃ ዝርዝር ያለበት ገጽ እና የጽ/ቤቱ ማህተም ሳይቆረጥ ፕሪንት በማድረግ ዘውትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00- 12፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ግልጽ እና ሀራጅ ሰነድ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በጽ/ቤታችን የእለት ገቢ ገንዘብ ሰብሳቢ ቢሮ ቁ.ር 16 ሰነድ የገዛበትን ደረሰኝ (RV) በመቀበል ዋጋ የሞሉበትን ሰነድ፣ ሌሎች ከላይ የተገለጹ አስፈላጊ ሰነዶች እንዲሁም RV (ሰነድ የተገዛበት ደረሰኝ) ጭምር በማያያዝ ወደ ጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) እንዲሁም በሃራጅ ጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎችንም በተመለከተ ማስያዝ ያለባችሁ የሲ.ፒ.ኦ መጠን በየኮዱ የሚለያይ ስለሆነ ከጨረታ ደንብ ላይ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በጉምሩክ ኮሚሽን በሞያሌ ቅርንጫፍ ስም በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ሚካሄደው በሞያሌ ቅ/ጽ/ቤት ሲሆን ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ባሉበት ወይም ታዛቢ ፊት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ማስታወቂያ በጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር እስከ 7ተኛው ቀን ድረስ ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች ናሙና በሞያሌ እና በሁሉም መጣቢያ የሚገኙ መጋዝኖቻችን እየሄዱ መመልከት አለባቸው፡፡
- ጨረታው የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀሚሮ የሚቆጠር በ8ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው ከጠዋቱ 3፡45 (ሶስት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ) ተዝግቶ 4፡00 (አራት ሰዓት) ላይ ይከፈታል፡፡
- ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተገለጸው ጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀሚሮ የምቆጠር 8ኛው ቀን የስራ ቀን ሳይሆን ስቀር ጨረታው መዝጊያ እና መከፈቻ ቀን በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
- ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፍ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታውን ውጤት ከተገለጸ በ 3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ በተራ ቁጥር 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት C.P.O ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0464441415/0464441564 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Ethiopian Customs Commission Moyale Branch invites bidders to a public and auction sale of confiscated and foreclosed motorcycles, vehicle spare parts, clothing, electronics, communication equipment, cosmetics, cleaning supplies, household goods, fuel, food items, cereals, and other goods. Bidders must submit a renewed business license, VAT registration, tax clearance, and recent VAT activity certificate.
