Tender Detail

Tender Details

  • Company በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address , Phone: 0910909004/0915717461
  • Website
  • Deadline23 Oct 2026, 5:30 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 200.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityሲፒኦ በሎት፡ ከብር 3,000 እስከ 58,200 (ዝርዝሩ በሰንጠረዡ)
  • opening dateበማግስቱ 3፡30 ሰዓት
  • Categories Textile, Garment & Leather , Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials

የደንብ ልብስ፣ የፅህፈት፣ የጽዳት፣ ቋሚ እቃዎች፣ የትራንስፖርት፣ የጥገና፣ የህትመትና ሌሎች አገልግሎቶች ግዥ (12 ሎቶች, 001/2019) - በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥው መለያ ቁጥር 001/2019

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1 የደንብ ልብስ የሲፒኦ መጠን = 55,500 ብር
ሎት 2 የፅህፈት እቃዎች የሲፒኦ መጠን = 40,000 ብር
ሎት 3 የጽዳት እቃዎች የሲፒኦ መጠን = 58,200 ብር
ሎት 4 ቋሚ እቃዎች የሲፒኦ መጠን = 33,570 ብር
ሎት 5 የጭነት አገልግሎት የሲፒኦ መጠን = 7000 ብር
ሎት 6 የትራንስፖርት አገልግሎት የሲፒኦ መጠን = 13,000 ብር
ሎት 7 ፈርኒቸር ጥገና የሲፒኦ መጠን = 12,000 ብር
ሎት 8 ኤሌክትሮኒክስ ጥገና የሲፒኦ መጠን = 12,000 ብር
ሎት 9 የተለያዩ ግብርና ግብአት የጓሮ አትክልት አይነቶች /ዘር/ የሲፒኦ መጠን 27,000 ብር
ሎት 10 የህትመት አገልግሎት የሲፒኦ መጠን 24,000 ብር
ሎት 11 የመኪና የወንበር ልብስ/ዲኮሬሽን/ 15,000 ብር
ሎት 12 የዲኮር እና ድንኳን ስራ አገልግሎት የሲፒኦ መጠን = 3000 ብር

ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

  1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው 1ኛ. ፋይናንሻል ኦርጅናል ለብቻ 2ኛ.ፋይናንሻል ኮፒ ለብቻ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ቲን ነምበር፣ ቫት፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት፣ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ እና የመሳሰሉትን ሰነዶች በሶስት ፖስታ ለየብቻ በማሸግ በድርጅቱ ሃላፊ /ተወካይ /ተፈርሞበት የድርጅቱን ማህተም በሰነዱ እና በፖስታው ላይ በመምታት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ፋይናንስ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በተራ ቁጥር አንድ መሰረት ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በፋይናንስ ጽ/ቤት 2ተኛ ፎቅ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የገዙትን መሙያ ሰነድ ሙሉ በሙሉ መመለስ ያስፈልጋል፡፡ ሰነዱን ቆርጦ ማስቀረት፣ ከተቀመጠለት መሙያ ቦታ ውጭ መሙላት፣ ስርዝ ድልዝ አድርገው ፊርማ አለመፈረም እና ማህተም በእያንዳንዱ ገፅ ላይ አለማድረግ ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
  5. የጨረታው ሳጥን በ10ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ 3፡30 ሰዓት ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት1፣ ሎት2 እና ሎት3 ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለቀሩት ሎቶች በቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ሲሆን በቀረበው የፍላጎት መግለጫ መሰረት የተሟላ የፍላጎት መግለጫ ማዘጋጀትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሚቀርቡ ናሙናዎችም ተከፍተው የሚታዩ መሆናቸውን ተጫራቾች ማወቅ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. የዘገየ ጨርታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
  9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ ጥያቄ፡-
አድራሻ ሃና ማሪያም ቀለበት ሳይሻገር ቆጣሪ ት/ቤት አጠገብ
ስልክ ቁጥር፡- 0910909004/0915717461/0913450134

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The administration seeks to procure uniforms, stationery, cleaning supplies, fixed assets, transport, maintenance, printing, and other services across 12 lots. Eligible bidders must submit financial originals and copies separately, renewed business license, TIN, VAT, supplier certificate, and bank-verified CPO in three sealed envelopes. Samples required for lots 1–3.
Save Tender