በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በባሌ ዞን የሚአ ጋሳራ የባለብዙ ቀበሌዎች መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለዋናው ፅ/ቤትና ከስሩ ላሉ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች የሚያገለግሉ የጽህፈት መሳሪያዎች ቋሚና አላቂ ዕቃዎች፣ የግንባታ እቃዎች (የውሃ)፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ፈርኒቸሮች ሞተር ሳይክሎች (ሳይክሎች) ጎማዎች፣ የደንብ ልብስና የደንብ ልብስ ስፌት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የሚኦ ጋሳራ የባለብዙ ቀበሌዎች መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 1/2019
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በባሌ ዞን የሚአ ጋሳራ የባለብዙ ቀበሌዎች መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለዋናው ፅ/ቤትና ከስሩ ላሉ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች የሚያገለግሉ የጽህፈት መሳሪያዎች ቋሚና አላቂ ዕቃዎች፣ የግንባታ እቃዎች (የውሃ)፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ፈርኒቸሮች ሞተር ሳይክሎች (ሳይክሎች) ጎማዎች፣ የደንብ ልብስና የደንብ ልብስ ስፌት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁም መሰረት :-
- ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል የሚያስችል በሚወዳደሩበት ዘርፍ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣የዘመኑን ግብር ከፍለው ያሳደሱ ፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) ብር የያዘ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን ሰነዶች ኦርጅናል እና ኮፒ ፣ በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
- አቅራቢው ድርጅት ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5/አምስት የስራ ቀናት ውስጥ በመስሪያ ቤቱ በአካል ቀርቦ ውል መፈራረም ይኖርበታል።
- ተወዳዳሪዎች በሚያቀርቡት ማንኛውም መረጃ ላይ ፊርማና ህጋዊ ማህተም ሊኖረው ይገባል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር / በባሌ ዞን ውሃ እና ኢነርጂ ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ በሚገኘው የሚኦ ጋሳራ የባለብዙ ቀበሌዎች መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 በመምጣት ወይንም MULTIPLF KEBELES MIO GASERA P/W/SEV በሚል ስም ወደ ተከፈተው የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000516045877 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በማስገባት ሰነዱን ከቢሮ ቁጥር 4 መወሰድ ይችላሉ።
- ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
አድራሻ ሮቤ ባሌ ከተማ
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0916117302/0913540425 ደውለው ይጠይቁ።
የሚኦ ጋሳራ የባለብዙ ቀበሌዎች መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
✨ messages.ai_summary
Supply of stationery, construction/water materials, electronics, furniture, motorcycles, tires, and uniforms for the Mio Gasera water utility. Bidders need a valid trade license, tax clearance, VAT and TIN.
