በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ሜንቴናንስ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ቶጋ
የደቡብ ዕዝ ሜንቴናንስ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የማስታወቂያ ቁጥር ደ/ዕዝ ሜንቴናንስ ግዥ B-01/2019 ዓ/ም
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ሜንቴናንስ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- የተለያዩ ሞዴል ያላቸው ቶዮታ ተሽከርካሪዎች የመለዋወጫ ዕቃ
- የተለያዩ ሞዴል ያላቸው ኮመርሻል ከባድ ተሽከርካሪዎች የመለዋወጫ ዕቃ
- የተለያዩ ሞዴል ያላቸው የመኪና ጎማዎች እና ባትሪዎች
- ለጦር መሳሪያና የጦር መሳሪያ ለጫኑ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች የሚውል አላቂ የጋራዥ መስሪያ ዕቃዎች
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች በጨረታው ሊወዳደር ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው የጨረታ ዓይነቶች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ /ከፋይነት/ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ለእያንዳንዱ ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መመሪያ መሠረት በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የዕቃውን ዓይነት ኤንቨሎፕ ላይ በግልፅ መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከተጫራቾች ዝርዝር መመሪያ ጋር የማይመለስ ብር 500.00 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታውጀ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት የሥራ ቀናት ውስጥ ቶጋ መከላከያ ሠራዊት ካምፕ በሚገኘው የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ሜንቴናንስ ግዥ ቢሮ መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቶጋ መከላከያ ሠራዊት ካምፕ በሚገኘው ደ/ዕዝ ጠ/መምሪያ 1ኛ ፎቅ ላይ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ደ/ዕዝ ጠ/መምሪያ 1ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈፅሙ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ያሸነፉበትን ዕቃ በራሳቸው ትራንስፖርት ወጭ በማጓጓዝ እና በማራገፍ ቶጋ መከላከያ ሠራዊት ካምፕ በሚገኘው የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ሜንቴናንስ ግምጃ ቤት ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ እንዲሁም 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 328 0019 /0988990839/ ይደውሉ
የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ሜንቴናንስ ቶጋ
✨ messages.ai_summary
The Ministry of National Defense Southern Command Maintenance invites legal bidders to supply spare parts for various Toyota and commercial heavy vehicles, tires, batteries, and consumable garage items for military vehicles. Bidders must have a valid trade license, supplier registration, tax clearance, VAT registration, and TIN.
