የፅህፈት መሳሪያ፣ ጽዳት፣ ደንብ ልብስ፣ ህትመት፣ የቢሮ እቃዎች፣ ጎማና ዘይት፣ የጥገና እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና እና መስተንግዶ ግዥ (10 ሎቶች) - የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት በመደበኛ ግልጽ ጨረታ ቁጥር የቂ/ከ/ከ/አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት 001/2019 ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ
- ሎት 1፡ የፅህፈት መሳሪያ
- ሎት 2፡ የጽዳት እቃዎች
- ሎት 3፡ የደንብ ልብሶች፣
- ሎት 4፡ የተለያዩ ቅርፃቅርጽና የህትመት ውጤቶችን
- ሎት 5፡ ቋሚና አላቂ የቢሮ መገልገያ እቃዎች
- ሎት 6፡ የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎች የመኪና ዘይትና ቅባቶች
- ሎት 7፡ የተለያዩ የጥገና እቃዎች
- ሎት 8፡ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች
- ሎት 9፡የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ የጥገና ስራዎች እና
- ሎት 10፡- የመስተንግዶ ግዥ /ውሀ ሌሎችም ወዘተ…በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች በገንዘብ ሚኒስቴር በእቃ አቅራቢዎች ዝርዝርና በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እንዲሁም በ2019 ዓ.ም በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ ለመሆናቸው ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና በዳግም ምዝገባ የተመዘገቡ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ከሚሸጡበትን ዋጋ 10% /አስር በመቶ/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ስም በማስያዝ የጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን እቃዎች አይነት ለመለየት የሚያስችል እቃዎች ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ታክስን ያካተተ መሆን አለበት፤
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ የእቃው አገልግሎት መጠንና ዋጋ / Financial & Techinical envelop በዝርዝር ተሞልቶ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለዚሁ ጨረታ ሲባል በተዘጋጀው ሳጥን የግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ማስገባት አለባቸው፤
- የጨረታው ሳጥን ማስታወቂያ በወጣው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ተዘግቶ በነጋታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰባተኛ ፎቅ አዳራሽ ይከፈታል፤
- የተጠቀሰው ቀን በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000009412399 በቅ/ጽ/ቤቱ ስም ገቢ በማድረግና አድቫይስ ይዞ በመምጣት የጨረታ ሰነድ መውሰድ የሚቻል ሲሆን የጨረታ ሰነዱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የቂርቆስ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ቢሮ የማስገባት ግዴታ አለበት፤
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች ቅ/ጽ/ቤቱ መጋዘን ወይም ስቶር ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፤
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ቄራ ኢትፍሩት ፊት ለፊት መንግድ ተሻግሮ ባለው መንገድ ወደ ውስጥ 50 ሜትር ገባ ብሎ ቅድስት ታወር
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን የቂርቆስ ክ/ከ/አነ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት የፋይናንስና ግዥ የስራ ሂደት
ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ የስልክ ቁጥር 011 4 70 16 63
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Procurement of stationery, cleaning supplies, uniforms, printing, office supplies, tires and oils, maintenance items, electronics repair, and catering, split into 10 lots. Open to bidders with a renewed trade license, tax compliance, MoF supplier registration, VAT registration, and a bid security of 10% of the total offer.
