የፅሕፈት መሳሪያ፣ የፅዳት እቃዎች፣ ህትመት፣ የህንፃ መሳሪያ፣ የመኪና መለዋወጫና ጎማ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የደንብ ልብስና የስፖርት ትጥቅ ግዥ - የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የፃግብጅ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የፃግብጂ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የፃግብጅ ወረዳ ገን/ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የፅሕፈት መሳሪያ፤ የፅዳት እቃዎች፤ ህትመት፤ የውሃ እቃዎች ፤ የህንፃ መሳሪያ፤ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፤ የመኪና ጎማ፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፤ የፈርኒቸር ውጤቶች፣ የደንብ ልብስ ፤ የስፖርት ትጥቅ፤ በግልፅ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል ። ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በየዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN)
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነ
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን "ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒዩ ወይም ጥሬ ገንዘቡን ከፖስታው ጋር ማያያዝ አለባቸው
- የእቃዎቹን አይነት ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን ከ 28/01/2019 እስከ 07/02/2019 11፡30 ድረስ ሰነድ መግዛት የሚቻል ሲሆን በ08/02/2019 3፡30 ድረስ የገዙትን ሰነድ በማስገባት በ 08/02/2019 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል ። ጨረታው የሚከፈተው ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን በሰዓቱ ካልተገኙ ጽ/ቤቱ በሌሉበት የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጆች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል ።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- ጨረታው ስርዝ ድልዝ ወይም የማይነበብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህግና ደንቦች በግዥ መመሪያ ቁጥር 144/2018 ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታውን ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የፃግብጅ ወረዳ ገን/ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Procurement of stationery, cleaning materials, printing, water supplies, building tools, vehicle spare parts and tires, electronics, furniture, uniforms, and sports equipment for the district's offices. Bidders must have a renewed trade license, tax payment proof, TIN, and VAT registration.
