የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለበረራ መስተንግዶ (onboard passenger service) እና ለስካይላይት ሆቴል አገልግሎት የሚውል የተጣራ ማር ከሚያመርቱ ድርጅቶች ጋር በኮንትራት ስምምነት ለሦስት (3) ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመስራት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:- SSNT-T648
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለበረራ መስተንግዶ (onboard passenger service) እና ለስካይላይት ሆቴል አገልግሎት የሚውል የተጣራ ማር ከሚያመርቱ ድርጅቶች ጋር በኮንትራት ስምምነት ለሦስት (3) ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመስራት ይፈልጋል:: ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ:-
- በአገልግሎቱ ዘርፍ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ ለ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ምዝገባ ወረቀት ያለው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ ፣ አንድ (1) ዓመትና እና ከዛ በላይ የስራ ልምድ ያለው ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ሁለት መቶ ብር (ብር 200.00) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T648 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ቅጂውን (scan copy) በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሶስት መቶ ሺህ ብር (300,000.00) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ ተቋም እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም::
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው:: ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኘው የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን በ 9:00 ሰዓት ይከፈታል::
ለተጨማሪ ማብራሪያ -
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
ስልክ ቁጥር: 011-517-4552
ወ/ሮ ብርቱካን ሰሙ
ኢ-ሜይል:birtukans@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
✨ messages.ai_summary
Ethiopian Airlines Group seeks producers of pure honey to supply onboard passenger service and Skylight Hotel under a three-year contract. Eligible bidders must hold a valid business license, renewed for 2018 E.C., a TIN certificate, VAT registration, and at least one year of relevant experience.
