Tender Detail

Tender Details

  • Company Ministry of Foreign Affairs
  • Address , Phone: 00 00 00 00
  • Website
  • Deadline12 Oct 2026, 5:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200(ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Securityለእያንዳንዱ ጨረታ 25,000 ብር (ሲ.ፒ.ኦ/ በጥሬ ገንዘብ)
  • opening dateይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ ስራ ቀናት
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በካዛንቺስ ባስገነባው አዲስ አፓርትመንት ህንፃ በሙሉ (ሙሉ ህንፃውን) ማከራየት ለሚፈልጉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ፣ ኩባንያዎች ወይም ፍላጎት ላላቸው አካላት በኪራይ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

Ministry of Foreign Affairs


የጨረታ ማስታወቂያ

ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የአፓርትመንት ህንፃ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በካዛንቺስ ባስገነባው አዲስ አፓርትመንት ህንፃ በሙሉ (ሙሉ ህንፃውን) ማከራየት ለሚፈልጉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ፣ ኩባንያዎች ወይም ፍላጎት ላላቸው አካላት በኪራይ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

የሕንፃው ዝርዝር መግለጫ

  • አድራሻ ካዛንቺስ፣ አዲስ አበባ
  • የወለል መጠን ምድር ስር 2 ወለል (B+2) + ሜዛኒን + ምድር + 18 ወለል (G+18)
  • የመኖሪያ አፓርትመንቶች (በአጠቃላይ 150 ክፍሎች)

-ባለ 3 መኝታ አፓርትመንት፡ 24 ክፍሎች
-ባለ 2 መኝታ አፓርትመንት፡ 42 ክፍሎች
-ባለ 1 መኝታ አፓርትመንት፡ 48 ክፍሎች
ስቱዲዮ (Studio) አፓርትመንት 36 ክፍሎች

ተጨማሪ አገልግሎቶች

  • የራሱ ግቢ ያለው (Own Compound)
  • ጄኔሬተር (Standby Generator)
  • መኪና ማቆሚያ የሚሆኑ 2 ምድር ወለሎች (B+2 underground Parking)
  • በግራውንድ እና ሜዛኒን ወለሎች ላይ ለቢሮ፣ ለንግድ፣ ለባንክ ወይም ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውሉ ሰፊ ቦታዎች

የመወዳደሪያ መስፈርቶች

  • ተወዳዳሪዎች ህጋዊ የድርጅት ምዝገባ/ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የውክልና ሰነድ ማቅረብ አለባቸው።
  • ፍላጎት ያላቸው ተቋማት ሙሉ ህንፃውን ለመከራየት የሚያስችላቸውን የፋይናንስና የቴክኒክ ፕሮፖዛል በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሠረት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  • ተወዳዳሪዎች የታዘዘውን የጨረታ ማስከበሪያ CPO ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማያያዝ አለባቸው።
  • መረጃና የቦታ ጉብኝት፡- ፍላጎት ያላቸው አካላት የህንፃውን ዝርዝር ፕላን ለመመልከት፣ የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ እና ህንፃውን በአካል ተገኝተው ለመጎብኘት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ ስራ ቀናት በሥራ ሰዓት ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ።

አድራሻ፡- ሂልተን ሆቴል ፊት ለፊት አዲሱ ህንፃ 3ኛ ወለል፣ ስልክ ቁጥር ፡- +251115531782/+251930470796/+251978738565

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

✨ messages.ai_summary
The Ministry of Foreign Affairs seeks to rent out its entire newly built apartment building in Kazanchis, Addis Ababa, for various services. The building includes 150 residential units, own compound, standby generator, and two underground parking floors. Open to international organizations, diplomatic community, companies, or interested parties.
Save Tender