የአዋሬ ጤና ጣቢያ ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በአንደኛ ዙር ጨረታ የሚያስፈልጉትን በዋናነት የጽሕፈት እና የጽዳት ዕቃዎች፣ እንዲሁም ሌሎች ቋሚ የሥራ መገልገያ መሳሪያዎችን (ፈርኒቸር እና ኤሌክትሮኒክስ) እና የቢሮ ዕቃዎች እንዲሁም የጥገና ሥራዎችን እና የጥገና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በምድብ (በሎት) ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአራዳ ክ/ከተማ የአዋሬ ጤና ጣቢያ
የአንደኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር - አ/ጤ/ጣ - 001/2019
የአዋሬ ጤና ጣቢያ ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በአንደኛ ዙር ጨረታ የሚያስፈልጉትን በዋናነት የጽሕፈት እና የጽዳት ዕቃዎች፣ እንዲሁም ሌሎች ቋሚ የሥራ መገልገያ መሳሪያዎችን (ፈርኒቸር እና ኤሌክትሮኒክስ) እና የቢሮ ዕቃዎች እንዲሁም የጥገና ሥራዎችን እና የጥገና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በምድብ (በሎት) ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጽሕፈት መሳሪያዎችን፣ የደምብ ልብሶችን፣ የጽዳት ዕቃዎችን፣ ቋሚ ዕቃዎችን፣ ህትመቶችን እና ሌሎች የሥራ መገልገያ መሳሪያዎችን፣ የጥገና ሥራዎችን እና የጥገና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ሥራዎችን በጥራት ለማቅረብ ወይም ለመሥራት የሚያስችል በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የ2019 ዓ.ም የንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የመንግሥት ግዢ ኤጀንሲ ድህረ-ገጽ ላይ በዘርፉ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ በግልጽ የሚታይ የምስክር ወረቀት ኮፒውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ከግብር ነጻ ስለመሆናቸው መልቀቂያ (ክሊራንስ) እና ሌሎች አስፈላጊ ዶክመንቶችን ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያሲዙት የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የሲፒኦ ሰነድ /ብር 11,000.00/ አስራ አንድ ሺህ ብር/ በአዋሬ ጤና ጣቢያ ስም በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ (ሲፒኦ) ብቻ ከዋናው የጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ ታሽጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር የሥራ ቀናት የቴክኒካል እና የፋይናንሺያል ሰነዶቻቸውን ኦሪጅናል እና ኮፒ እንዲሁም የሲፒኦ ሰነድ በኦሪጅናል ሰነድ ውስጥ በማድረግ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከላይ በተገለጸው ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 403 በመምጣት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ጥቃቅን እና አነስተኛ ማይክሮ ኢንተርፕራይዝ ተጫራቾች በሀገር ውስጥ እና በራሳቸው በሚያመረቱት ዕቃዎች ላይ ብቻ ካደራጃቸው ተቋም ለመስ/ቤታችን የዋስትና ደብዳቤ ከሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ የዋጋ ዝርዝር ሞልተው ማቅረብ እንጂ በሌላ ሰነድ ከሞሉ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የተፈለገውን ዕቃ ሳይሰርዙ፣ ሳይጨምሩ እና ሳይቀንሱ ለተጠቀሰው አገልግሎት ወይም ዕቃ ዋጋውን ብቻ በዋጋ መሙያው ላይ መሙላት አለባቸው፤ ይህን ያላደረገ ተጫራች ከጨረታ ውድድሩ ይሰረዛል፡፡
- ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ዝርዝር ላይ ቫት /VAT/ ማካተት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚጫረቱበትን የመወዳደርያ ዋጋ ሞልተው በታሸገ ፖስታ ውስጥ አድርገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሞላው ነጠላ ዋጋ ነው፡፡
- ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- አዋሬ፣ አዋሬ ጤና ጣቢያ ጎን ኮከብ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ፊትለፊት 4ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0118688278 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የአዋሬ ጤና ጣቢያ
✨ messages.ai_summary
Aware Health Station seeks suppliers for stationery, cleaning materials, furniture, electronics, office supplies, and maintenance works/electronics, split into lots via open bid. Bidders need a valid 2019 business license, supplier registration certificate, VAT/tax registration and clearance, samples where required, and must be micro/small enterprises for locally produced goods.
