በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት በ 2019 በጀት ዓመት ለድርጅቱ ስራ ማስፈጸሚያ የሚውሉና ቀጥለው የተዘረዘሩትን እቃዎችን በብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Gosh Meda Pipe & Plastic Manufacturing Enterprise (የጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት)
ብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ጨ/001/2019
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት በ 2019 በጀት ዓመት ለድርጅቱ ስራ ማስፈጸሚያ የሚውሉና ቀጥለው የተዘረዘሩትን እቃዎችን ማለትም :-
| ሎት | የጨረታው ዓይነት |
| 1. | የቢሮ አላቂ እቃዎችን (የጽህፈት መሳሪያዎችን) |
| 2. | የደንብ ልብስና ተዛማጅ ቁሳቁሶችን |
| 3. | የጽዳት እቃዎችን (ሌሎች አላቂ እቃዎችን) |
| 4. | ለምርት ማምረት ስራ የሚያገለግሉ አላቂ እቃዎችን |
በብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ድርጅቱ ይገብዛል::
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊና አግባብነት ያለው ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ያላቸው፣
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የማመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸው::
- የሚገዙ የእቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን / ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶችን ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 500.00/ አምስት መቶ ብር/በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ጎሽሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት ደሴ/ገራዶ ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ / ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ /ቫቱን/ ጨምሮ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው ደረቅ ቼክ ማስያዝ አይቻልም::
- አንድ ተጫራች በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት የዕቃ አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይቻልም። ሆኖም በሎቱ ውስጥ ከተዘረዘሩት ዕቃዎች ውስጥ አንድ ዕቃ ዋጋ ሳይሰጥበት ቢቀር ተጫራቹ ድርጅት ከጨረታ ውጪ የሚሆን ይሆናል::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን /ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት ቢሮ ቁጥር 6 በመገኘት ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት ቢሮ ቁጥር 6 ጨረታው በጋዜጣ በወጣበት በ21ኛው ቀን ከረፋዱ 4:30 ላይ በይፋ ይከፈታል::
- ድርጅቱ ጨረታውን የሚያወዳድረው በሎት ነው::
- ድርጅቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- በጨረታው ተወዳደሮ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች ድርጅቱ ወደሚገኝበት ደሴ ገራዶ አግሪስቶን ቅጥር ግቢ ድረስ የሚያቀርብ ይሆናል::
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0962999933/0914601139/ 0914052633 /0991841910/0930878784 በመደወል ወይንም በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል::
አድራሻ: ደሴ/ ገራዶ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ደሴ የግንባታ ግብዓት ማምረቻ ማዕከል ቅጥር ግቢ
የጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት
✨ messages.ai_summary
Gosh Meda Pipe & Plastic Manufacturing Enterprise seeks suppliers for office stationery, uniforms and related materials, cleaning supplies, and production consumables, awarded by lot. Bidders must hold a valid trade license, tax payment proof, TIN, and VAT registration if the purchase exceeds ETB 200,000.
