Tender Detail

Tender Details

  • Company በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
  • Address ሸገር ከተማ ፣ኢትዮጲያ, Phone: 0924113872
  • Website
  • Deadline11 Oct 2026, 5:30 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100(ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Securityከጠቅላላ ዋጋ 1% (CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ)
  • opening dateበነጋታው በ4፡30 ሰዓት
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials , Electronics Materials

የቋሚ፣ አላቂ፣ የፅህፈት መሳሪያ፣ የፅዳት፣ የደንብ ልብስ እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ – በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት

በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በ2019 የበጀት አመት የተለያዩ ቋሚ፣ አላቂ፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ሕጋዊ ድርጅቶች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ከ100,000ብር ለሆና ግዥ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  3. በገንዘብና ትብብር ልማት ሚኒስቴር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፈቃድ ሰጪ አካላት በአቅራቢነት የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች ብቻ መካፈል ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት በማይመለስ 100 ብር መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ፍ/ቤቱ ካቀረበው መስፈርት /standard/በታች ማቅረብ አይቻልም፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም፡፡
  7. ፍ/ቤቱ የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች ብዛት እንደ አስፈላጊነታቸው (50%) በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላል፡፡
  8. ጨረታው የሚቆየው ለተከታታይ 15 ቀናት ይሆናል፡፡ በ15ኛው ቀን 11፡30 ተዘግቶ በነጋታው በ4፡30 ሰዓት ተጫራቶቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
  9. ማንኛውም ተጨራች በጨረታ ተካፋይ ለመሆን ተመላሽ የሚሆን ባቀረበው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 1% የጨረታ ማስከበርያ /CPO/ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  10. ፍ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ፍ/ቤቱ የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች ብዛት ለተከታታይ 6 ወራት ውል ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ይዋዋላል፡፡
  12. የሚገዙ ዕቃዎች በተሠጠው እስፔስፊኬሽን መሠረት ተሞልተው ካልቀረቡና ማንኛውም ዓይነት ስህተት ቢፈፀም ሃላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ነው፡፡

አድራሻ፡ ቱሉ ዲምቱ አደባባይ የንሳ [?] የሚወስደው መንገድ አሲክስ ተብሎ የሚጠራ አካባቢ የሚገኝ የፍርድ ቤቱ ቢሮ 5ቁጥር የፋይናንስ ክፍል ያገኙናል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ 09-24-11-38-72

በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት

✨ messages.ai_summary
Sheger City High Court's Koye Feche district court seeks suppliers for durable and consumable goods, stationery, cleaning supplies, uniforms, and electronics via open tender. Eligible bidders must hold a valid business license, be tax-compliant, VAT-registered for purchases above 100,000 birr, and registered as suppliers with the Ministry of Finance or relevant authority.
Save Tender