Tender Detail

Tender Details

  • Company በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስ/የወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ቃሊቲ ከአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ወረድ ብሎ ውሃ ልማት አጠገብ የወረዳው ጽ/ቤት ሁለተኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0913382003
  • Website
  • Deadline07 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200( ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Securityበየሎቱ: ከብር 2,000 እስከ 30,000 (CPO)
  • opening dateበ11ኛው ቀን 4፡30
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials , Cloth And Shoes

የፅዳት፣ የፅህፈት መሳሪያ፣ የደንብ ልብስ፣ ቋሚ እቃዎች እና ሌሎች (10 ሎቶች) ግዥ – የጨረታ ቁጥር 001/2019 – በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስ/የወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ እቃዎች ዝርዝር 

ሎት-1 የፅዳት እቃዎች፣ ሎት-2 የፅህፈት መሳሪያ፣ ሎት-3 የደንብ ልብስ፣ ሎት-4 ቋሚ እቃዎች፣ ሎት-5 የትራንስፖርት አገልግሎት፣ ሎት-6 ዘር ግብአት፣ ሎት-7 አላቂ እቃ፣ ሎት-8 መድረክ ማስዋብ፣ ሎት-9 የተሽከርካሪ ጎማ፣ ሎት-10 የቢሮ መስተንግዶ

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን አሟልቶ በግልፅ ጨረታ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

  1. ተጫራቾች በንግድ ምዝገባ የተመዘገቡና በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ከሃገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀትና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር ሁለት መቶ (200.00) በመክፈል በአቃ/ቃ/ክ/ከ/ወ5 ፋይናንስ ጽ/ቤት ሁለተኛ (2ኛ) ፎቅ መውሰድ ይችላሉ፡፡
    ሎት የእቃው/አገልግሎቱ አይነት የጨረታ ማስከበሪያ (ብር)
    ሎት-1 የፅዳት እቃዎች 10,000
    ሎት-2 የፅህፈት መሳሪያ 10,000
    ሎት-3 የደንብ ልብስ 15000
    ሎት-4 ቋሚ እቃዎች 30,000
    ሎት-5 የትራንስፖርት አገልግሎት 5,000
    ሎት-6 ዘር ግብአት 5,000
    ሎት-7 አላቂ እቃ 10,000
    ሎት-8 መድረክ ማስዋብ 2,000
    ሎት-9 የተሽከርካሪ ጎማ 5,000
    ሎት-10 የቢሮ መስተንግዶ 5,000

    ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በየሎቱ ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ ኖርባቸዋል።

  3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ ቃሊቲ ከአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ወረድ ብሎ ከውሃ ልማት ጎን በሚገኘው ወረዳ 5 ፋይናንስ/ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ (200.00) ሁለት መቶ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ። ተጫራቾች የወሰዳችሁትን የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በማሸግ ኢንቨሎፕ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  5. ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡
  6. የጨረታው መክፈቻ ቀን በ11ኛው ቀን ሆኖ ነገር ግን 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ወይም በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰአት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  7. የጨረታው አሸናፊ ጽ/ቤቱ ባቀረበው መጠን ወይም ብዛት እቃዎችን ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፈበት የጠቅላላ ዋጋ 10% ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል በአነስተኛና ጥቃቅን የተደራጀ ከሆነ አምራች የሆነ ብቻ ሲሆን አምራች መሆኑና የሚያመርተው እቃ ተጠቅሶ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  9. ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉት በጨረታው ሰነድ ላይ በተጠቀሰው ስፔስፊኬሽን ሞዴል መሰረት ብቻ ነው፡፡
  10. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን እቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከሁለት ቀናት በፊት የማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራቾች በሚያቀርበው እቃ (ናሙና ላይ የተለየ ምልክት ወይም የድርጅቱን ማህተም ማድረግ የተከለከለ ነው ፡፡
  12. እያንዳንዱ ሰነድ ላይ ማህተም እና የሞሉት የዋጋ ማቅረቢያ ላይ የተጫራቾች ፊርማና የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡
  13. የጨረታው አሸናፊ ውል ከተፈጸመበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበት እቃ በሙሉ በራሱ ትራንስፖርትና ሰራተኛ በማውረድና በማጓጓዝ ባቀረበው ናሙና መሰረት በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለንብረት ክፍል ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
  14. ለሚገቡ የቋሚ እቃዎች ለአንድ ዓመት ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  15. ሰነዱን ሲሞሉ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
  16. ስርዝ ድልዝ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡ እንዲሁም ለአንድ እቃ ከአንድ ዋጋ በላይ ማቅረብ አይፈቀድም።
  17. ዋጋ ተወደደብኝ እቃው ጠፋብኝ ማለት የማይቻል መሆኑ መታወቅ ያለበት መሆኑና ያስያዙት ሲፒኦ የሚወረስ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ቃሊቲ አሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ወረድ ብሎ ውሃ ልማት አጠገብ የወረዳው ጽ/ቤት ሁለተኛ ፎቅ ፋይናንስ ጽ/ቤት ይገኛል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0913382003 /0923286082/ 0923481386

በአቃቂ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Procurement of cleaning supplies, stationery, uniforms, fixed assets, transport services, seeds, consumables, event decoration, vehicle tires, and office catering across 10 lots. Open to registered domestic bidders with a valid trade license, tax clearance, supplier registration, and VAT certificate. Samples required before bid opening.
Save Tender