የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን የደንብ ልብስ (የሥራ እና የአደጋ መከላከያ አልባሳት እና ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መስያ ቁጥር ኢ.አ-ኮ/ብግጨ/05/2019
የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን የደንብ ልብስ (የሥራ እና የአደጋ መከላከያ አልባሳት እና ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት ጨረታውን መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ የምስከርወረቀት የሚያቀርቡ ግብር የመከፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንደዚሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ እና መመዝገባቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) አዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ ባንኮች የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ስም በማሰራት ማቅረብ ይችላሉ፡፡ ከኢንሹራንስና ከፋይናንስ ተቋማት ውጪ የሚቀርቡ ዋስትናዎች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ ስለዚህ የጨረታ ማስከበሪያውን ከቴክኒክሰነድ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
| ሎት | የምድብ ዝርዝር | የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ (በኢትዮጵያ ብር) |
| 1 | የደንብ ልብስ (የሥራ እና የአደጋ መከላከያ አልባሳት | 70,000 |
| 2 | አደጋ መከላከያና የመጀመሪያ የህከምና ዕርዳታ ቁሳቁስ | 25,000 |
- የጨረታ ሰነዱን የሚፈልጉ ተጫራቾች መረጃ ለማግኘት አጠቃላይ የግዥ አቅርቦት ቢሮ ብሎክ አንድ ሁለተኛ ፎቅ የግዥ፣ንብረት እና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት ዳይሬክተር ኢኢኮ ጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች በተቀመጠው አድራሻ በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 እና ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 10፡00፣ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 5፡30 እና ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 10፡00 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በሁለት የተለያየ ኢንቨሎፖች (ቴክኒካል የመወዳደሪያ ሀሳብ እና ፋይናንሻል የመወዳደሪያ ሀሳብ) ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከታች በተገለፀው ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ በሚገኝበት ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊ ሆነው ከተመረጡ የውል ማስከበሪያ የአሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውን እና ድርጅታቸውን ማህተም ማስፈር አለባቸው፡፡
- ኮርፖሬሽኑ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ሕንጻ 1፣ ሁለተኛ ፎቅ ፡ በግዥ ንብረትና ፋሲሊት አስተዳደር የጠቅላላ ግዥ አቅርቦት ዲቭዥን ቢሮ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ከመገናኛ አደባባይ ወደ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሚወስደው የቀለበት መንገድ ወደ ኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት ማእከል (አደይ አበባ ስታዲየም) በሚያስገባው መገንጠያ መንገድ አጠገብ አዲሱ መሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት የሚሰጥበት ህንጻ.
የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን
✨ messages.ai_summary
Ethiopian Engineering Corporation seeks to buy work and protective clothing and safety/first-aid materials via open tender. Bidders must have a valid trade license, VAT registration, tax clearance, supplier registration, and submit samples for each item. Bids go in two envelopes (technical and financial).
