በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በአቃቂ ቃሊቲ ከ/ከተማ ጤና ፅ/ቤት የሰላም ፍሬ ጤና ጣቢያ በ 2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል ስለሆነም በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የሰላም ፍሬ ጤና ጣቢያ
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ሰ/ፍ/ጤ/ጣ/ግ/ጨ/001/2019
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በአቃቂ ቃሊቲ ከ/ከተማ ጤና ፅ/ቤት የሰላም ፍሬ ጤና ጣቢያ በ 2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል ስለሆነም በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡፡
- የቢሮ የፅህፈት መሳሪያዎች 2 አላቂ የፅዳት ዕቃዎች 3 የደንብ ልብሶች 4 ቋሚ ዕቃዎች 5.የጥገና፣የቧንቧ እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች 6.የህትመት ስራዎች 7.የተለያዩ የቢሮ ማስዋቢያ የሚያገለግሉ ዕቃዎችን 8.የመኪና ጎማን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ሀጋዊ የንግድ ፍቃድ ያወጡና የተሰጣቸው ንግድ ፈቃድ 1(አንድ) ዓመት የሞላው ከሆነ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No) ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በወጣው ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ዘውትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 እና ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 11፡30 4ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 45 የግገዢና ንብረት አስተዳደር ክፍል በአካል በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ ለሚገዛቸው ዕቃዎች ማለትም በጨረታ ሰነዱ ላይ በከፍል 6 ላይ የተዘረዘሩትን የዕቃዎችና ተያያዥ አገልግሎቶች ዝርዝር መግለጫ ላይ ናሙና ሳምፐል/ እንድታቀርቡ በተጠየቀው መሠረት የተጠየቁትን ናሙና /ሳምፕል/ የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት ቢሮ ቁጥር 45 የግዥ የስ/ሂደት እንድታስገቡ እየገለጽን ናሙና (ሳምፕል) ያልቀረበባቸው እቃዎች ውድቅ እንደሚሆኑባችሁ አውቃችሁ ለምትወዳደሩበት እቃዎች በሙሉ ናሙና(ሳምፕል) እንድታቀርቡ እያሳሰብን የምታቀርቡትን ናሙና/ሳምፕል/ በተመለከተ ጤና ጣቢያው የራሱን ኮድ የሚሰጥ በመሆኑ በምታቀርቡት ናሙና ሳምፕል ላይ የድርጅታችሁን ስም መጻፍ ወይም መለጠፍ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ በተጨማሪም ከጽዳት ዕቃዎች የእጅ ሳሙና፣ የልብስ ሳሙና፣ ሶፍት፣ በረኪና፣ ዲቶል እና ኦሞ፣ ከቢሮ የጽህፈት መሳሪያዎች መካከል እርሳስ፣ እስኪርብቶ፣ ፍሉድ፣ ኡሁ፣ ማርከር እና የማህተም ቀለም የጤና ጣቢያው የጥራት ኮሚቴው ዕቃዎቹን ከፍቶ ጥራቱን የሚፈትሽ(የሚመረምር/ መሆኑን በጥብቅ ያሳውቃል ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን እና ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማርኛ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ CPO ከጨረታ ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባችኃል፡፡ ለእያንዳንዱ ሎት የምታቀርቡት CPO መጠን የእንደሚከተለው ይሆናል፡-
- የደንብ ልብሶች 6211- 44.720.00 (አርባ አራት ሺህ ሰባት መቶ ሀያ ብር ብቻ)
- አላቂ የቢሮ እቃዎች6212:- 47.000.00 (አርባ ሰባት ሺህ ብር ብቻ)
- የተለያዩ የህትመት ስራዎች6213:- 20,968.27 (ሀያ ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ስምንት ብር ከ 27/00 ሳንቲም
- አላቂ የጽዳት ዕቃዎች6218:- 51,000.00 (ሀምሳ አንድ ሺህ ብር ብቻ)
- የጥገና እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች6219:- 1,000.00 (አስራ አንድ ሺህ ብር ብቻ)
- ቋሚ ዕቃዎች6313:- 60,000.00 (ስልሳ ሺህ ብር ብቻ)
- የተለያዩ የቢሮ ማስዋቢያ የሚያገለግሉ ዕቃዎች 6314- 6,000.00 (ስድስት ሺ ብር ብቻ)
- የመኪና ጎማ 6241 - 14.849.88 (አስራ አራት ሺህ ስምንት መቶ አርባ ዘጠኝ ብር ከ ሰማኒያ ስምንት ሳንቲም)
- ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ መስጠት የተከለከለ ሲሆን ነገር ግን ይህ ሆኖ ቢገኝ ከጨረታ ውጪ ይሆናሉ፡፡
- የጨረታው ዋጋ ለ2 ወር ጸንቶ ይቆያል ይህም ሲሆን ገዥና ሻጭ ተስማምተው እስከ ቀጠሉ ድረስ ለ6 ወራት ድረስ በስምምነት ይቆያል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በሚመለከት አንድ ኦርጅናል አንድ ኮፒ መቅረብ አለባችሁ፡፡
- ተጫራቾች በተሰጣቸው የዋጋ መሙያ ሠነድ ላይ ምንም ዓይነት ስፔስፊኬሽን መጨመርም ሆነ መቀነስ አይችሉም፡፡
- ከጥቃቅን እና አነስተኛ ወይም ካደራጃቸው መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ይዘው የሚጫረቱ ተጫራቶች ከሆኑ ምን አይነት ምርት እንደሚያመርቱ እና የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሀገር ውስጥ ምርት ችርቻሮ ጅምላ ንግድ ከሆነ ደግሞ ከአምራቹ የተሰጣቸውን ፍቃድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ካልሆነ ግን እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ በመግዛት እና የጨረታ ማስከበሪያ፡ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሰነድ ጤና ጣቢያው የማይቀበልና ከውድድር ውጭ የሚያደርግ መሆኑን ይገልጻል፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኃላ ተጫራቶች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይቹሉም፡፡ በተጨማሪም ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቶች ከጨረታው ውጭ ሆነው ለወደፊቱም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ ይደረጋሉ፡፡ እንዲሁም ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ይወረስባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ በመለየትና በፖስታው ላይ በመግለጽ በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ጤና ጣቢያው ግቢ ቢሮ ቁጥር 45 ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሳጥኑ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ይታሸግና በማግስቱ ከጠዋቱ 4፡ 00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው በሚከፈትበት ቦታ፤ ቀንና ሰዓት በራሳቸው ምከንያት ባይገኙ የጨረታ ሳጥኑ እንዲከፈት በማድረግ ውድድሩ ይካሄዳል፡፡
- በጨረታው ላይ ሁለት እና ከሁለት በላይ የሆኑ እጩ ተወዳዳሪዎች በግምገማው እኩል ውጤት ካቀረቡ ቅድሚያ ለሀገር ውስጥ አምራች ለሆኑ ዕድሉን የምንሰጥ ሲሆን የሀገር ውስጥ አምራች ተወዳዳሪ ካሌለ አሸናፊውን በእጣ የምንለይ ይሆናል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች የግዢ ውል እንዲፈጽም ከመ/ቤቱ ደብዳቤ ከደረሰው ከቀናት በኃላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የአቅርቦት ውል ከግገዢ ፈጻሚ መ/ቤቱ ጋር መፈራረም አለበት፡፡ የውል ግዴታ ካልተወጣ በቀጣይ ከመንግስት ግዢ እንዲታግድ ይደረጋል፡፡
- ገዢው መ/ቤት በጨረታ ማስታወቂያ የተጠየቀውን ዕቃ ካቀረበው መጠን /ብዛት/ላይ 20% ከውል በፊት የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
- አቅራቢው በገባው የውል ስምምነት መሰረት የዕቃውን ዓይነት፣ መጠን እና ጥራት ጠብቆ በውሉ ላይ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ካላቀረበ የግዢ ፈጻሚ መ/ቤቱ በጨረታ ሰነዱ በከፍል 8 በልዩ የውል ሁኔታዎች ላይ በተገለጸው መሠረት አሸናፊ ተጫራች ካሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 0.01% በየቀኑ ዕቃውን እስከሚያስረከብበት ቀን ድረስ ተቀናሽ ሆኖ ለመስሪያቤቱ የጉዳት ካሳ ገቢ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም አቅራቢው ያሸነፈበትን ዕቃ ፈጽሞ ካላቀረበ ያስያዘው የውል ማስከበሪያ 10% መ/ቤቱ ይወርሳል፡፡
- በግዢ ፈጻሚ መ/ቤት እና በአቅራቢው መካከል የተለየ ስምምነት ከሌለ በስተቀር የተያዘው የውል ማስከበሪያ ዋስትና አቅራቢው ግዴታውን ሙሉ በሙሉ እንደተወጣ ሲረጋገጥ ወዲያውኑ ተመላሽ
- በጨረታ ሂደቱ ላይ ጉዳት ደርሶብኛል ወይም በጨረታ ግምገማ ውጤት ላይ ቅር የተሰኘ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በድጋሜ እንዲታይለት የጨረታ ውጤት ይፋ ሆኖ በማስታወቂያ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን በግዢ ፈጻሚ መ/ቤት የበላይ ኃላፊ በጽሁፍ ቅሬታውን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ሆኖም
✨ messages.ai_summary
The Addis Ababa City Administration Akaki Kaliti Sub-City Health Office, Salame Fere Health Station, seeks to purchase office stationery, cleaning supplies, uniforms, fixed assets, maintenance/plumbing/electrical items, printing services, office decoration items, and vehicle tires via open tender. Bidders must hold a valid renewed business license, TIN, VAT registration, and supplier registration, and submit samples.
