Tender Detail

Tender Details

  • Company ፋና ቦሌ ሸማቾች ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኀበር
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251 9 65 44 88 88
  • Website
  • Deadline30 Sep 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 300 /ሶስት መቶ ብር/
  • Bid Securityብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በባንከ በተረጋገጠ CPO
  • opening dateበስምንተኛው ቀን 4፡00
  • Categories Food And Beverage , Food Items And Drinks , Stationery Materials

በፋና ቦሌ ሸማቾች ኃላፊነቱ የተወሰነ ሕብረት ሥራ ማህበር በ2019 ዓ.ም በዓመት ውስጥ የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ፋና ቦሌ ሸማቾች ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኀበር


የጨረታ ማስታወቂያ

በፋና ቦሌ ሸማቾች ኃላፊነቱ የተወሰነ ሕብረት ሥራ ማህበር በ2019 ዓ.ም በዓመት ውስጥ የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የሎት ቁጥር የዕቃው ዝርዝር
1 ሎት 1 የስቴሽነሪ እቃዎች
2 ሎት 2 የበግ ስጋ አቅራቢዎች
3 ሎት 3 እንስሳትና የእንስሳት ተዋፅኦ አምራቾችና አከፋፋዮች (ወተት፣ ቅቤ፣ አይብ፣ እንቁላል እና አሳ)
4 ሎት 4 ሚጥሚጣ እና የበርበሬ ቅመም ግዥ
5 ሎት 5 የዕዳት እቃዎች
6 ሎት 6 ከሰል አቅራቢ
7 ሎት 7 የኳስ ሜዳ ሳር እድሳት ከነ ባለሙያው
  1. በዘርፉ የታደሠ ህጋዊ የንግድ የሥራ ፈቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብርከፋይነት መለያ ቁጥር፣ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ወቅታዊ የግብር ከፍያ ማረጋገጫ፣ የቫት/የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ እንዲሁም ሎት 2 ፣ ሎት 3 ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ሰርተፊኬት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በባንከ በተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች ሠነድ ሊወስዱ ሲመጡ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/በመከፈል ሠነድ መግዛት ይኖርባቸዋል፤
  4. ከላይ የተዘረዘሩ መረጃዎችና ሰነዶች አሟልተው በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሰባት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ እስከ 11፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው በስምንተኛው ቀን 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ሻላ 17/17 ህብረተሰብ ልማት ማዕከል ይከፈታል፡፡ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታ ሣጥን መከፈቻ ሥነ-ሥርዓትን አያስተጓጉልም፡፡
  6. አሻሚ፣ የተሰረዘ፣ የተደለዘ እና ግልፅ ባልሆነ ሁኔታ የጨረታ ዋጋ በመሙላት መወዳደር ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፤
  7. የሚወዳደሩባቸውን እቃዎችና ናሙና ጨረታው በሚከፈት ቀን በዝርዝር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. በጨረታው አሸናፊ ለሆኑባቸው ዕቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 2% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከድርጅቱ ጋር የግዥ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል፡፡
  9. በዓመት ውስጥ ሊገዙ የታሰቡትን ግብዓቶች ዓመታዊ ትስስር ይፈፅማል፡፡
  10. የጨረታውን መመሪያ አለማክበር ከጨረታው ያሰርዛል፤
  11. ፋና ቦሌ ሸማቾች ኃላ/የተ/የህ/ሥ/ማህበር ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- የፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/የህ/ሥራ ማህበር 17/17 ህብረተሰብ ልማት ማዕከል ሻላ መናፈሻ ቅጥር ግቢ ውስጥ የማዕከሉ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቀርበው ሠነዱን መግዛት ይቻላል፡፡

ስልክ ቁጥር 0116184076/0116187529/0116631244

ፋና ቦሌ ሸማቾች ኃላ/የተ/የህ/ሥ/ማህበር

✨ messages.ai_summary
Fana Bole Consumers' Cooperative Union seeks suppliers via open tender for stationery; sheep meat; animal products (milk, butter, cheese, eggs, fish); mitmita and berbere spices; debt-related items; charcoal; and football field grass renovation with experts. Bidders need valid trade license, registration, TIN, tax clearance, VAT registration; lots 2 and 3 require Food and Drug Authority certificate.
Save Tender