Tender Detail

Tender Details

  • Company ኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ሰበታ ካምፓስ
  • Address Oromia Ethiopia, Phone: ------
  • Website
  • Deadline26 Sep 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር200.00 (ሁለት መቶ ብር) የማይመለስ
  • Bid Securityብር30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት CPO ብቻ
  • opening dateበተጠቀሰው ቀን 4፡30
  • Categories Furniture And Furnishing , Cleaning & Janitorial , Office Supplies And Services

ኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ሰበታ ካምፓስ ለ2019 በጀት ዓመት ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ ሎት1፣ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ አላቂ ዕቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ ሎት 2 የመኪና ጎማዎችን፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ሰበታ ካምፓስ


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2019

ኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ሰበታ ካምፓስ ለ2019 በጀት ዓመት ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ ሎት1፣ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ አላቂ ዕቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ ሎት 2 የመኪና ጎማዎችን፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይገልጻል፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና እንዲሁም የሚፈለግባቸውን የዘመኑን ግብር አጠናቀው ስለመከፈላቸው በቂ ማስረጃ (ከሊራንስ) ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለእያንዳንዱ ሎቶች የማይመለስ ብር200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል ከካምፓሱ ሂሳብና በጀት ቢሮ ቁጥር 12B መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የአቅራቢነት ምስከር ወረቀት እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎቶች በተዘጋጀው ሰነድ ብር30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት CPO ብቻ ኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ሰበታ ካምፓስ ስም አዘጋጅተው ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት CPO በጀርባው የባንኩን ማህተም እና ስልክ ቁጥር ከሌለው ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  6. ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኋላ የሚሸጡበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ (15%) በመጥቀስ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ ሰነድ ለየብቻ በማሸግ በተባለው ቀን ውስጥ ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ለጨረታ በሚያቀርቡት በእያንዳንዱ የሰነዱ ገጽ ላይ የድርጅቱን ስምና አድራሻ የሚገልጽ ሕጋዊ ማህተምና ፊርማ ማስፈር አለበት፡፡
  9. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት መሥሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ቦታ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃዎች ገቢ የሚሆነው አስፈላጊውን ጥራት ማሟላቱን በባለሙያ እና ጥራት አጣሪ ኮሚቴ ሲረጋገጥ ብቻ ይሆናል፡፡
  11. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ በመጋዘን ቀድመው ማከማቸት ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ የሎት አንድ(1) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙናውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
  13. የጨረታው ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የሥራ ቀናት የሚሸጥ ሆኖ በ16ኛው ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ቀን 4፡30 የሚከፈት ይሆናል፡፡
  14. በዚህ ጨረታ አሸናፊ የሆነ ተጫራች (ድርጅት) የሚያስገባውን ዕቃ ዋጋ ከመቶ አስር10 ፐርሰንት የማስያዝ ግዴታ አለበት፡፡
  15. ከላይ የተገለጸው የመከፈቻ ቀን በዓል ወይንም የሰንበት ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በቀጣዩ የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  16. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0113383638/0925586338/

ኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ሰበታ ካምፓስ

✨ messages.ai_summary
Oromia State University Sebeta Campus invites bids for Lot 1: educational materials, stationery, cleaning supplies, consumables, and uniforms; Lot 2: vehicle tires, electronics, and furniture. Bidders must hold a valid trade license, tax clearance, supplier certificate, TIN, and VAT registration.
Save Tender