Tender Detail

Tender Details


የአየር አምባ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋ/ግ/ን/አስ/የስራ ሂደት በጨረታ ቁጥር አየ/አ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት 01/2019 መሰረት የ2019 በጀት ዓመት ለመማር ማስተማሩ የሚውሉ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2019

የአየር አምባ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋ/ግ/ን/አስ/የስራ ሂደት በጨረታ ቁጥር አየ/አ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት 01/2019 መሰረት የ2019 በጀት ዓመት ለመማር ማስተማሩ የሚውሉ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የጨረታ ግዢ መለያ ቁጥር አየ/አ/2ኛ/ደረጃ ት/ቤት 01/2019

ተ.ቁ የእቃውና አገልግሎቱ አይነት የግዥ ሎት ምድብ የግዥው ምድብ የጨረታው ማስከበሪያ የብር መጠን
1 የአላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች ሎት 1 እቃ 10,000 00
2 የደንብ ልብስ ሎት2 እቃ 10,000 00
3 የፅዳት እቃዎች ሎት3 እቃ 15,000 00
4 የፈርኒቸር እቃዎች ሎት4 እቃ 10,000 00
5 የኤሌክትሮኒክስና ኤሌክትሪክ እቃዎች ሎት5 እቃ 15,000 00
6 የህንፃ መሳሪያ እቃዎች ሎት6 እቃ 10,000 00
7 የስፖርት እቃዎች ሎት7 እቃ 10,000 00
8 ህትመት ሎት8 አገልግሎት 6,000 00
9 የደንብ ልብስ ስፌት ሎት9 አገልግሎት 5,000 00
10 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና ሎት10 አገልግሎት 4,000 00
11 መፅሃፎችና የትምህርት መረጃ መሳሪያዎች ሎት11 እቃ 8,000 00
12 የፍሳሽ ማስወገድ/ ሽንት ቤት ማስመጠጥ/ ሎት12 አገልግሎት 3,000 00
13 የውሃ መስመሮች ጥገና ሎት13 አገልግሎት 3,000 00
14 የፈርኒቸር እቃዎች ጥገና ሎት14 አገልግሎት 3,000 00
15 የትራንስፖርት አገልግሎት ሎት15 አገልግሎት 3,000 00
16 ኬሚካሎችና የላብራቶሪ የትምህርት መሳሪዎች ሎት 16 እቃ 10,000 00

ከሎት ቁጥር 8 – 15 የተጠቀሱት የአገልግሎት ግዢዎች በበጀት ዓመቱ አገልግሎቱ በሚፈለግበት ወቅት በሚታዘዘው መጠን ልክ ሲሆን ውሉ ጸንቶ የሚቆየው እስከ በጀት አመቱ መዝጊያ መሆኑን እናሳውቃለን።

  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆነ፤ የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገቡ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል እና በ2018ዓ.ም በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆናቸው ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ አካል የተሰጣቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት።
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት አለባቸው።
  3. ከአቅራቢዎች ስም ዝርዝር ውስጥ በተለያዩ ጥፋቶች ያልተሰረዙ ወይም የቅጣት ጊዜያቸው ያልተጠናቀቀ በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ አይችሉም፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት እቃ ከላይ በየሎቱ በተቀመጠው መሰረት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ CPO ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። CPO ሲዘጋጅ በአየር አምባ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ስም መሆኑን እንገልፃለን።
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ለማስገባት በሚመጣበት ጊዜ ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች አብሮ ማስገባት አለበት ሳምፕል ለማቅረብ ምቹ ያልሆኑ እቃዎችን በፎቶ ማቅረብ ግዴታ ሲሆን ሳምፕል ያላቀረበ ተጫራች የጨረታውን ሰነድ የማናወዳድር መሆኑን በቅድሚያ ት/ቤቱ ይገልጻል።
  6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እንዲሁም CPO ከኮፒው ሰነድ ጋር በታሸገ ኢንቨሎፕ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ እና በፊርማ በማረጋገጥ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-11፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በማግስቱ ማለትም በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት በአየር አምባ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በቢሮ ቁጥር 4 ይከፈታል።
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ሲቀመጥ ቫትን ያካተተ መሆኑ መገለጽ አለበት።
  8. በጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ (10%) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ CPO ማስያዝ ይኖርበታል።
  9. ት/ቤቱ አሸናፊው ተጫራች ያቀረበው ዋጋ ሳይቀየር 20% መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል።
  10. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ ውል ከተፈራረመበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ እስከ ት/ቤቱ ንብረት ክፍል በራሱ ትራንስፖርት ማድረስ ይኖርበታል።
  11. ት/ቤቱ በጨረታው የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. በማስታወቂያው ላይ ያልተገለጹ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል።
  13. ለሎት 15 የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ 2% ተመዝጋቢ የሆነ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል መወዳደር ይችላል።

አድራሻ፡- በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር ቦሌ ሚካኤል ሩዋንዳ ኤምባሲ ጀርባ 500ሜትር ገባ ብሎ ለበለጠ መረጃ ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት ቀናት ውስጥ ዘውትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር፡- 011-822 0132 / 011-822 0137 ላይ በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

የአየር አምባ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Ayir Amba Secondary School seeks suppliers for educational materials and services across 16 lots, including stationery, uniforms, cleaning supplies, furniture, electronics, sports equipment, printing, tailoring, maintenance, transport, books, and laboratory chemicals. Bidders must hold a valid trade license, VAT registration, tax clearance, and supplier registration.
Save Tender