የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለሠራተኞች የስራ ልብስ የሚሆን ሎት 1፡- የተዘጋጀ የሥራ ልብስ (ጃኬትና ሱሪ) እና ሽርጥ እንዲሁም ሎት 2፡- ጓንት እና መጥረጊያ፣ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለሠራተኞች የስራ ልብስ የሚሆን ሎት 1፡- የተዘጋጀ የሥራ ልብስ (ጃኬትና ሱሪ) እና ሽርጥ እንዲሁም ሎት 2፡- ጓንት እና መጥረጊያ፣ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት፡-
- በእያንዳንዱ ሎት ላይ በትከከለኛው የስራ መስክ የተሰማራና የንግድ ስራ ፈቃዱን ያሳደሰ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው
- የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሎት 1፡- 20.000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ሎት 2፡- 10.000.00 (አስር ሺህ ብር) ለሁሉም ሎቶች ለእያንዳንዳቸው ከላይ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን ለየብቻው በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፈርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርመና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው
- በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፤ ካለም አንድ ሰረዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
- በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት እቃዎች መካከል ከፋፍሎ ወይም ቀንሶ መወዳደር አይቻልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች አሪጅናል የጨረታ ሰነድ ለሁሉም ሎቶች ለየብቻ ኦርጅናል ፓስታ በማዘጋጀት እና በጥንቃቄ ለየብቻ በማሸግ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ሁለቱንም ሎቶች በጠ /በአንድ/ ፖስታ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- አንድ ተጫራች የንግድ ሥራ መስኩ ከፈቀደለት በሁሉም ሎቶች ወይም የሚፈልገውን ሎት ብቻ መርጦ መወዳደር ይችላል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ጨረታው በተዘጋበት ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ ውስጥ በይፋ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ከመከፈት አይታገድም፡፡
- የመክፈቻ ቀኑ የህዝብ በዓል ወይም እሁድ ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች አሸናፊ መሆኑ ሲገለፅለት የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ያስይዛል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት /የጨረታ ሰነድ/ ለየብቻ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል ከካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- አቅራቢ ድርጅቱ የማስጫኛ እና የማስወረጃ እንዲሁም ሌሎች ወጪዎችን ሸፍኖ ንብረቱን ለካምፓኒው ንብረት ከፍል ያስረክባል፡፡
- ካምፓኒው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበስጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-011637 58 03 ደውለው ይጠይቁ
የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር ደ/ብርሃን
✨ messages.ai_summary
The association seeks to buy employee workwear via open tender: Lot 1 prepared workwear (jacket, trousers, sweater) and Lot 2 gloves and mops. Bidders must be licensed in the field, have a TIN, and be VAT-registered. Bids must be submitted separately per lot; partial bidding within a lot is not allowed.
