Tender Detail

Tender Details

  • Company መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር
  • Address አዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 03 በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም ከጠበል መድኃኒአለም ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0930796413
  • Website
  • Deadline21 Sep 2026, 10:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 400 (አራት መቶ ብር ብቻ)
  • opening dateበዚሁ ዕለት በ5፡00 ሰዓት
  • Categories Disposal Sale , Other Sales , Used Items

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ሰነድ ቁጥር 130

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ቁሳቁሶቹም፡

  1. ያገለገሉ ጎማዎች
  2. የተለያዩ የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች
  3. ያገለገሉ የስፖንጅ ፍራሾች
  4. የብረት ገዳዎች (ዲፖዎች)፤ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችና ቶቦላሬዎች /ስክራፕ/
  5. የተነቃቀሉ ጣውላዎች
  6. የማካሮኒና የፓስታ መጠቅለያ ማሽንና ጀኔሬተሮች
  7. ያገለገሉ ወንበሮች

በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾ አዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03፣ (በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም፣ ከጠበል መድኃኔዓለም ቤተክርስያን ፊት ለፊት) በሚገኘው በማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ቁሳቁሶቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት ከተመለከቱ በኋላ በማዕከሉ የጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ድረስ በመምጣት ብር 400 (አራት መቶ ብር ብቻ) በመከፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡

የጨረታ ሰነዱ ለሽያጭ የተዘጋጁትን ቁሳቁሶች ዝርዝር የያዘ ሲሆን ዕቃዎቹን እየተዘዋወሩ ከተመለከቱ በኋላ በሰነዱ በእያንዳንዱ ቁጥር አንፃር የተለዩትን ዕቃዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት እና ዕቃውን ለመግዛት ያስገቡትን ዋጋ 10% ለጨረታ ማስከበሪያ ከያዘ ሲ.ፒ.ኦ ጋር በማያያዝ ካሸጉ በኋላ የጠቅላላ አገልግሎት ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጧቱ በ4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ5፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ከኛው ቀን እሁድ ወይም ብሔራዊ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ

ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0989-90-90-51 ወይንም 0975-26-41-59 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር

✨ messages.ai_summary
Macedonia Charity Association invites bids to buy used items from its compound, including used tires, assorted electronics, used sponge mattresses, scrap metal, recycled timber, macaroni/pasta packing machines, generators, and used chairs. Bidders must inspect items and obtain the tender document.
Save Tender