የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከዚህ በፊት መለየት ቁጥር DBE/NCB/CGPSD/02/2026 በግልጽ ጨረታ አውጥቶ የነበረ ሲሆን ነገር ግን በድጋሚ ግልጽ ጨረታ የጋርመንት ማሽኖች ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር DBE/NCB/CGPSD/03/2026
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከዚህ በፊት መለየት ቁጥር DBE/NCB/CGPSD/02/2026 በግልጽ ጨረታ አውጥቶ የነበረ ሲሆን ነገር ግን በድጋሚ ግልጽ ጨረታ የጋርመንት ማሽኖች ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ከማሽነሪዎቹ የአገልግሎት ባህሪ መሰረት ተጫራቾች ከንዑስ ክፍል 1-3 ያሉት ላይ ለመሳተፍ ከእያንዳንዱ ክፍል ቢያንስ አንድ ማሽነሪ ላይ መጫረት ግዴታ ሲሆን፤ በቀሪዎቹ ከንዑስ ክፍል 4-6 ያሉት ላይ ግን በተናጠል ወይም በጅምላ እንደፍላጎታቸው ለመሳተፍ ይችላሉ፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-
- ተጫራቾች የታደሰ የቀበሌ/የፋይዳ መታወቂያ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የቀረጥ ነጻ መብት ያላቸው ወይም ቀረጥ ከፍለው መስተናገድ የሚፈልጉ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚሳተፉበትን የማሽነሪዎች ድምር ዋጋ 25 (ሀያ አምስት በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (ሲፒኦ) ወይም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ስም በጨረታው ዕለት ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ተጫራቶች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት መስከረም 36 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በባንኩ 3ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡
- አሸናፊው ያስያዘው ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ጋር ሲታሰብለት፣ ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
- የተዘረዘሩትን አቃዎች የጨረታው አሸናፊ እቃዎቹን እንዲያነሳ ከተነገረው በኋላ በአስር (10) የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡
- ማሽነሪዎቹን መመልከት የሚፈልጉ ተጫራቶች ገላን ከተማ በሚገኘው የባንኩ መጋዘን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር ቅዳሜ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10:00 ሰዓት በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ፦ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የካፒታል ዕቃዎች ግዢና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ስልክ ቁጥር፡ +251-85-24-44-90 ወይም ኢ-ሜይል: egpsd2026@dbe.com.et መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
✨ messages.ai_summary
Ethiopia Development Bank invites bidders to a public tender for the sale of government machinery. Bidders must bid on at least one machine from each of sub-categories 1–3, and may bid separately or in bulk on sub-categories 4–6. Renewed kebele/fayda ID required; duty-free or duty-paid bidders eligible.
