Tender Detail

Tender Details

  • Company በለሚ ኩራ ክፍስ ከተማ ወረዳ 06 የአብዲ ጃርሶ ቅድመ ስንደኛ ፣አንደኛና ደረጃ ት/ቤት
  • Address Addis Ababa Ethiopia, Phone: ------
  • Website
  • Deadline07 Sep 2026, 5:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን በየሎቱ ይለያያል።
  • opening dateበ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30
  • Categories Cleaning & Janitorial , Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 የአብዲ ጃርሶ ቅድመ እንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለመስራት ይፈልጋል፡፡

በለሚ ኩራ ክፍስ ከተማ ወረዳ 06 የአብዲ ጃርሶ ቅድመ ስንደኛ ፣አንደኛና ደረጃ ት/ቤት


ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር C01/2018

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 የአብዲ ጃርሶ ቅድመ እንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለመስራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሚመለከታቸው ድርጅቶች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት መስፈርቱን የሚያሟሉ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. የደንብ ልብስ
  2. ሌሎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
  3. የፅዳት ዕቃዎች
  4. ለፕላንት ለማሽነሪ እና ለመሳሪያ መግዣ
  5. የልብስ ስፌት
  6. ለህንጻ ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች መግዣ
  7. ለመስተንግዶ
  8. ህትመት ስራዎች
  9. ለትራንስፖርት አገልግሎት
  10. ልዩ ልዩ የኪራይ
  11. ለተለያዩ መሳሪያዎች እና መጸሐፍት
  12. ለፕላንት ለማሽነሪ እና ለመሳሪያ እድሳት እና ጥገና
  13. ለአላቂ ህክምና እቃዎች
  14. ለአላቂ የትምህርት ዕቃዎች
  15. ለህንጻ ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች እድሳት እና ጥገና

በጨረታ መሳተፍ ለምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባችሁ፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃቸውንና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆኑ የምስክር ወረቀትና ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና ህጋዊ ደረሰኝ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት 1 የደንብ ልብስ /50,000/ ሎት 2 ሌሎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎች /50,000/ ሎት 3 የፅዳት ዕቃዎች /50,000/ ሎት 4 ፕላንት ለማሽነሪ እና ለመሳሪያ መግዣ /50,000/ ሎት 5 የልብስ ስፌት /10,000/ ሎት 6 ለህንጻ ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች መግዣ /50,000/ ሎት 7 ለመስተንግዶ /10,000/ ሎት 8 የህትመት ስራዎች /10,000/ ሎት 9 ትራንስፖርት አገልግሎት /10,000/ ሎት 10 ልዩ ልዩ የኪራይ /10,000/ ሎት 11 ለተለያዩ መሳሪያዎች እና መጸሐፍት /10,000/ ሎት 12 ለፕላንት ለማሽነሪ እና ለመሳሪያ እድሳት እና ጥገና /10,000/ ሎት 13 ለአላቂ ህክምና እቃዎች /10,000/ ሎት 14 ለአላቂ የትምህርት እቃዎች /10,000/ ሎት 15 ለህንጻ ለተገጣጣሚዎች እድሳት እና ጥገና (ግንባት) /50,000/ ካደራጃቸው ወረዳ ደብዳቤ የቀረበ ዋስትና መሆን አለበት፤ ከሎት 1 እስከ ሎት 15 ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን እና በተባለው መሰረት በባንክ የተመሰከረለት /ሲፒኦ/ የተከፈለበት በአንዱ ከዋናው ዋጋ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰአት እስከ ቀኑ አስራ አንድ /11፡00/ ድረስ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 የአብዲ ጃርሶ ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 01 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች በእያንዳንዱ እቃ የሚጫረቱበትን ዋጋ ዝርዝር በመግለጽ ፖስታ ሰነዱን በአሪጂናልና ኮፒ በድርጅቱ ኩባንያ ማህተም በማድረግ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. የጨረታ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰአት ላይ ሳጥኑ ይታሸጋል፤ ስለዚህ ሁሉም ተጫራቾች ሰነዳቸውን አስገብተው ማጠናቀቅ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃዎች ዋጋ ሰነድ ሲያቀርቡ አሪጂናልና ደረጃውን የጠበቀ ናሙና በት/ቤቱ ግዥ ቢሮ ማድረግ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች ያቀረቧቸውን እቃዎች ተወዳድረው ካሸነፉበት ናሙና ምንም ለውጥ ሳያደርጉ በራሳቸው ወጪ ጭነው የማቅረብና ደረጃውን ያልጠበቀ እቃ ከሆነ መልሰው ትክክለኛውን እቃ የማምጣት ግዴታ አለባቸው፡፡
  9. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናንስ ት/ቤቱ ውስጥ ሲሆን ጨረታው ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰአት በአል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% /ሲፒኦ/ በቅድሚያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. በማንኛውም ግልጽ ጨረታ ላይ ያልታገዱ መሆን አለበት፡፡
  12. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ከቫት ጋር መሆን አለበት፡፡
  13. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ አቅራቢዎች የጨረታ ማስከበሪያ ሆነ የዋስትና ደብዳቤ ካደራጃቸው አካል በጽ/ቤት ኃላፊ በኩል ተፈርሞ የቀረበ ዋስትና መሆን አለበት፡፡
  14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ለሚ ኩራ ከ/ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር የአብዲ ጃርሶ ት/ቤት ልዩ ስሙ ቦሌ አራብሳ ጃርሶ ገባ ብሎ፡፡

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 የአብዲ ጃርሶ ቅድመ እንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for procurement of goods and services across 15 lots, including uniforms, office supplies, cleaning items, machinery, tailoring, construction materials, hospitality, printing, transport, rentals, equipment, medical and educational supplies, and renovation works. Bidders must hold valid licenses, tax clearance, VAT registration, and supplier registration.
Save Tender