ለትግል ለነፃነት ቅድመ እንደኛ፣ እንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም
ትግል ለነፃነት ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ለትግል ለነፃነት ቅድመ እንደኛ፣ እንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም
- የደንብ ልብስና የወንድ እና የሴት ጫማዎች
- አላቂ የፅዳት ዕቃዎችን
- የትምህርት የፅህፈት መሳሪያዎችን
- የቢሮ አላቂ ዕቃዎች
- የስፖርት ትጥቅ እና የስፖርት ዕቃዎች
- የኤሌክትሪክ ዕቃዎች
- የህንፃ መሳሪያዎች
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ፣ የቫት የምዘገባ ወረቀት አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ያሸነፉበትን ዕቃ ግዥ መ/ቤት ድረስ በራሳቸው ወጭ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቶች የአንዱን ዋጋ ሲያቀርቡ ከነቫቱ ደምረው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚመለስ ብር 300.00/ ሶስት መቶ/ ብር በመከፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ በመ/ቤቱ ሰነድ ብቻ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱ ማስገቢያ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ለተከታታይ ለ10 ቀናት ይሆናል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ዕቃዎችን ማስረከብ ያለበት ማሸነፉን ከተነገረው በ10 የስራ ቀናት ውስጥ ማስረከብ አለባቸው፡፡
- የጨረታው ማስገቢያ ት/ቤት ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት፡፡
- የጨረታውን ሰነድ ከላይ በተራ ቁጥር 4 የተጠቀሰውን ገንዘብ በመከፈል በት/ቤቱ ፋይ/ግ/ን/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 መውሰድ ይቻላል፡፡
- ጨረታው በወጣ በአስራ አንደኛው ቀን 4:15 አራት ሰዓት ከሩብ/ ታሽጎ 4:30 /አራት ሰዓት ተኩል/ ት/ቤቱ አዳራሽ ህጋዊ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል።
- ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱን የተጠበቀ ነው።
ለጨረታ ማስከበሪያ ብር ከታች የተገለፀውን በባንክ የተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነድ ጋር እያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡
የደንብ ልብስና የወንድና የሴት ጫማዎች ብር 3000/ሶስት ሺህ/፣ የአላቂ የፅዳት ዕቃዎች ብር 6000 /ስድስት ሺህ ብር/፣ የትምህርት እና የፅህፈት መሳሪያዎች ብር 5500/አምስት ሺህ አምስት መቶ ብር/ የቢሮ አላቂ ዕቃዎች በብር 5500/አምስት ሺህ ብር፣ አምስት መቶ/ ፤የስፖርት ትጥቆች እና የስፖርት ዕቃዎች ብር 4000/አራት ሺህ/፣ የኤሌከትሪክ ዕቃዎች ብር 4000/አራት ሺህ የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች ብር 4500/አራት ሺህ አምስት መቶ/ ፣የህንፃ መሳሪያዎች ብር4500 /አራት ሺህ አምስት መቶ/ እንዲሁም የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎች ብር 4000/አራት ሺህ ብር/
አድራሻ፦ ትግል ነፃነት ቅድመ አንደኛና አንደኛ መካከለኛ ደረጀ ትምህርት ቤት በየካ ክፍለ ከተማ በቀድሞ ቀበሌ 01/02 በአዲሱ ወረዳ 01 ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ሳይደርስ 800 ሜ ሲቀረው 41 ቁጥር አውቶቢስ መሄጃ መስመር
ማሳሰቢያ፡- ለጥራት 80% ለዋጋ 20% ስለሆነ ለጥራት ከምንም በላይ ቅድሚያ እንሰጣለን፡፡
☞ የአንዱን ዕቃ ዋጋ ስታቀርቡ ከነቫቱ ማቅረብ አለባችሁ።
☞ ቫት ሳያካትት ዋጋ ያቀረበ ድርጅት ጨረታው ወድቅ ይሆንበታል፡፡
☞ ማንኛውንም ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ ሲያስገባ ሳምፕል ማቅረብ አለበት።
ማንኛውም ተጫራች መረጃ መጠየቅ ሲፈልግ በስራ ቀናት ጠዋት 2፡30-11:30 ባለው ጊዜ ደውሎ መረጃ መጠየቅ ይችላል፡፡ ቅዳሜና እሁድ የእረፍት ቀናት ስለሆነ መ/ቤቱ ዝግ ነው።
ስልክ ቁጥር፡- 0111541611/0118120047
የትግል ስነፃነት ቅድመ አንደኛ፣ ስንደኛና መካከስኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
