Tender Detail

Tender Details

  • Company የሮቤ ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት
  • Address ሮቤ ከተማ : ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 34 86 64 74
  • Website
  • Deadline24 Aug 2026, 10:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 500.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityየጨረታ ዋጋ 20% (በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ)
  • opening dateበዚው ዕለት 5:00 ሰዓት
  • Categories Other , Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

ያገለገሉ ብረታ ብረቶች፣ የመንገድ ዳር ፖሎች እና ሌሎች ዕቃዎች ሽያጭ

የሮቤ ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት


ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1/2019

በሮቤ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማው የሚገኙ ያገለገሉ ብረታ ብረቶች፤ የመንገድ ዳር ፖሎች እና ሌሎች ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ሰነዱን መግዛት የምትችሉ ሲሆን፤

  1. መስሪያ ቤቱ አድረሻ፤ ሮቤ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስቶ ብር/ በመግዛት ከሮቤ ከተማ ገ/ጽ/ቤት ግዥ ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  2. ማንነቱን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስ መቶ ብር/ በግዛት ከሮቤ ከተማ ን/ጽ/ቤት ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ ዋጋ 20% /ሃያ በመቶ/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ በሮቤ ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ዋናውንና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከገዙበት ዕለት ጀምሮ ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች በሮቤ ከተማ ገልማ አባ ገዳ አዳራሽ በመገኘት በስራ ሰዓት ማየት ይችላሉ።
  7. የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ከ11ኛ ስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የጨረታው ሠነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ ከታሸገ በኋላ በዚያው ዕለት 5:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ እንደተረጋገጠ ያሸነፈበትን ዋጋ በሮቤ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የባንክ አካውንት ላይ ሙሉ በሙሉ ገቢ ሲያደርግ ያሸነፈውን ንብረት 15 ቀን ውስጥ ማንሳት አለበት፡፡
  9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

CPO ለማሰራት ሮቤ ከተማ ገንዘብ/ጽ/ቤት

ለበስጠ መረጃ ሮቤ ከተማ ገ/ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር፡- 0934866474/0912365294 መጠቅ የምትችሱ መሆኑን እንገልጻስን፡፡

የሮቤ ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for the sale of used metals, roadside poles, and other items in Robe City. Bidders must purchase tender documents and provide a renewed ID copy. Items can be inspected at Gelma Aba Geda Hall.
Save Tender