የተለያዩ አገልግሎት መስጠት የማይችሉ የመንግስት ቋሚ ንብረቶችን (የተማሪ የብረት አልጋዎች፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን፣ የተማሪ ወንበሮች እና የተለያዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎች) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ
በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ማህበራዊ ጥናት ኮሴጅ
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ማህበራዊ ጥናት ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ አገልግሎት መስጠት የማይችሉ የመንግስት ቋሚ ንብረቶችን የተማሪ የብረት አልጋዎች፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን የተማሪ ወንበሮች እና የተለያዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታ ለመሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፤
- ተጫራቾች ለ2018 ዓ/ም ከዘርፉ ጋር አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ እንዲሁም የዘመኑ ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከጨረታ ሰነድ ጋር ኮፒውን አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ ብቻ በኢት/ያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000554811454 ገቢ በማድረግ የባንክ አድቫይስ በማምጣት በኮሌጁ ግዥ ዴስክ ቢሮ ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ንብረቶቹን በማንኛውም የመንግስት የሥራ ሰዓት በኮሌጁ ግቢ ውስጥ በአካል መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የሚጫረቱበትን የንብረቱን ጠቅላላ ዋጋ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በጥንቃቄ በመሙላት የድርጅታችሁም ህጋዊ ማህተምና ፊርማ ማስቀመጥ ይኖርባችኋል።
- ተጫራቾች ዋጋ የተሞላበትን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ፖስታ አድርገው ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ ጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኢ/ያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ማህበራዊ ጥናት ኮሌጅ ውስጥ በሚገኘው ግዥ ዴስክ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4:00 ተዘግቶ በእለቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ ግዥ ዴስክ ቢሮ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) ጨረታው ሳይከፈት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ያስያዙትን ሲፒኦ የጨረታው አሸናፊ ከታወቀ ወዲያውኑ ለተሸናፊዎች የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊ ድርጅት ንብረቶቹን ጨርሶ ሲያነሳ የሚመለስለት ይሆናል።
- አሸናፊ ድርጅት የአሸነፈባቸውን ዕቃዎች በአጠቃላይ የማንሳት ግዴታ አለበት።
- ኮሌጁ ለአፈፃፀም የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ማህበራዊ ጥናት ኮሌጅ ሞጆ በቀጥታ ስልክ ቁጥር-0221162424 ጠይቆ መረዳት ይቻላል።
- ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎችን የነጠላ ዋጋ መስጠት አይቻልም። አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ዋጋ ድምር ነው፡፡
- ተጫራቾች የመንግስት ኤሌክትሮኒክስ ግዥ (EGP) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ማህበራዊ ጥናት ኮሌጅ
✨ messages.ai_summary
- Sale of unserviceable government fixed assets via open tender, including student metal beds, a photocopy machine, student chairs, and various office equipment.
- Issued by the Ethiopian Defense University, College of Business and Social Studies.
- Tender closes on Nehasse 20, 2018 E.C. at 4:00 AM; opening will take place the same day at 4:30 AM.
- Non-refundable bid document fee is ETB 200; bid bond is ETB 10,000 via bank-guaranteed CPO or cash.
- Bidders must hold a renewed 2018 E.C. trade license, provide proof of current tax payment, be registered on the Government Electronic Procurement (EGP) system, and submit a total lump-sum price only.
