Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲያደብርና ዋዩ ወረገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address AMHARA Ethiopia, Phone: 0116200679
  • Website
  • Deadline24 Aug 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300 ብር (ሎት 1)፣ 100 ብር (ሎት 2)፣ 200 ብር (ሎት 3)፣ 200 ብር (ሎት 4) - የማይመለስ
  • Bid Security40,000 ብር (ሎት 1)፣ 6,000 ብር (ሎት 2)፣ 15,000 ብር (ሎት 3)፣ 10,000 ብር (ሎት 4) - በሲፒኦ ወይም በህጋዊ ደረሰኝ /መሂ-1/
  • opening dateበዕለቱ ከጠዋቱ 4፡10
  • Categories Cleaning & Janitorial , Office Supplies And Services , Vehicle tire

የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የተሽከርካሪ ጎማ እና መለዋወጫ እቃዎችና የተሽከርካሪ ቅባትና ዘይት ግዥ

የሲያደብርና ዋዩ ወረገንዘብ ጽ/ቤት


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳደር የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፤ የጽዳት እቃዎች፤ የተሽከርካሪ ጎማ እና መለዋወጫ እቃዎችና የተሽከርካሪ ቅባትና ዘይት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች እንድትሳተፉ ይጋብዛል።

  • በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው /ያላት/፤
  • በዘርፉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው /ያላት/
  • ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ በተመሰከረለት ትክክለኛ ሲፒኦ ወይም በህጋዊ ደረሰኝ /መሂ-1/ ማስያዝ አለባቸው።

ሎትየጨረታው ዓይነትየጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋየጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና
1.የጽህፈት መሳሪያዎች30040,000
2.የጽዳት እቃዎች1006,000
3.የተሽከርካሪ ጎማ እና መለዋወጫ እቃዎች20015,000
4.የተሽከርካሪ ቅባትና ዘይት20010,000
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ድረስ ባሉት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከላይ የተጠቀሰውን የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ የማይመለስ ብር በመክፈል ከሲ/ዋዩ ወ/ገን/ጽ/ቤት ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 መግዛት ይችላሉ፡፡
  • ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለተጫራቾች ከፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡10 ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል።
  • ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ዋጋ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ምንም ስርዝ ድልዝ በመሙላት ኦርጅናሉን ብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በፖስታው ላይ ስማቸውን፣ አድራሻቸውን እና የሚወዳደሩበትን የጨረታ ዓይነት በመፃፍ ሲያ/ዋ/ወ/ገን/ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
  • አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጪ በማጓጓዝ በፑሉ በሚገኙ ንብረት ከፍል ገቢ ያደርጋል።
  • አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ካሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር በባንክ በተመሰከረ ትክክለኛ ሲፒኦ ወይም በህጋዊ ደረሰኝ /መሂ-1/ በማስያዝ ውል ይፈጽማል።
  • መ/ቤቱ በግዥው ላይ 20% የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
  • የጨረታ ውድድሩ በጥቅል ዋጋ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡
  • መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116200679 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
- Procurement of office supplies, cleaning materials, vehicle tires and spare parts, and vehicle lubricants and oils via open tender. - Issued by Siyadebrna Wayu Woreda Finance Office, Amhara Region. - Bid documents are non-refundable: Lot 1 – 300 ETB, Lot 2 – 100 ETB, Lot 3 – 200 ETB, Lot 4 – 200 ETB. Bid bonds: Lot 1 – 40,000 ETB, Lot 2 – 6,000 ETB, Lot 3 – 15,000 ETB, Lot 4 – 10,000 ETB (CPO or legal receipt/Mehi-1). - Submission closes on the 16th day at 4:00 AM; bids will be opened the same day at 4:10 AM. - Bidders must have a renewed trade license, tax identification number, and proof of VAT registration.
Save Tender