Tender Detail

Tender Details

  • Company AFRICA INSURANCE COMPANY S.C (አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ.)
  • Address ቦሌ ሩዋንዳ ድልድይ አካባቢ አፍሪካ ኢንሹራንስ ህንፃ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116 637485
  • Websitehttps://africainsurancesc.com/
  • Deadline17 Jul 2026, 3:00 PM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር)
  • opening date2026-07-17 15:30:00
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials , Construction Materials And Raw Materials

AFRICA INSURANCE COMPANY S.C (አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ.) የተለያየ መጠን ያላቸውን የፅህፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች እንዲሁም የህትመት ውጤቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

AFRICA INSURANCE COMPANY S.C (አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ.)


አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ /አ.ማ/

 

የፅህፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች እንዲሁም የህትመት ውጤቶች ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የጨረታ ቁጥር AICI-0015/2026

 

ኩባንያችን የተለያየ መጠን ያላቸውን የፅህፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች እንዲሁም የህትመት ውጤቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

ሀ. ሎት -1 የፅህፈት መሣሪያዎች

ለ. ሎት-2 የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ::

1.     ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ እንዲሁም ከሚመለከተው የመንግስት ተቋም የብቃጥ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::

2.     ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: የጨረታው አሸናፊ ባቀረበው ሰነድ መሰረት እቃዎቹን ሳያቀርብ ቢቀር ያስያዘው በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል ወይም ተመላሽ አይሆንም::

3.     ከላይ በተራ ቁጥር 2 ላይ የተገለጸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ሲፒኦ (CPO) ሙሉ ለሙሉ ተመላሽ የሚሆነው አሸናፊው ድረጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች ለኩባንያው ገቢ ካደረገ በኋላ ኩባንያው የገቡትን እቃዎች በሳምፕላቸው መሰረት መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ ነው::

4.     በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኩባንያው ዋና መ/ቤት በመገኘት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ::

5.     ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር መሆን ወይም አለመሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል::

6.     ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ሀምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሀምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ድረስ ቦሌ በሚገኘው የአፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ዋና መ/ቤት ህንፃ 11ኛ ፎቅ በስራ ሰዓት በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::

7.     ጨረታው ሀምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ዋና መ/ቤት ህንፃ 11ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የስብሰባ/ስልጠና አዳራሽ ይከፈታል::

8.     ተጫራቾች የሚያስገቡት የጨረታ ሰነድ የእቃው ዝርዝር መግለጫ (Specification) የያዘ ሊሆን ይገባል እንዲሁም በሚያቀርቡት ናሙና (Sample) ላይ የድርጅታቸው ማህተም ሊኖር ይገባል::

9.     አንዱ ተጫራች በሌላው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት ከጨረታው የሚያሳግድ መሆኑን እንገልፃለን::

10. አሸናፊው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተገለፀለት ወይም የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ የፅህፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች ከ7 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ወይም በውሉ መሰረት ማቅረብ ይኖርበታል::

11. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የፅህፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች ሲወዳደሩ ባስገቡት (ባቀረቡት) ሳምፕል / ናሙና እንዲሁም የህትመት ውጤት በኩባንያው ናሙና መሰረት መሆን አለበት::

12. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ እንዲሁም የህትመት ውጤቶች የኩባንያው ዋና መ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርባቸዋል::

13. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ በከፊል ወይም በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0116 611877 / 0116 637485 /0116 637716 በመደወል መጠየቅ ይቻላል::

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ድልድይ አካባቢ (ሸዋ ሱፐርማርኬት ፊት ለፊት) አፍሪካ ኢንሹራንስ ህንፃ

 

Save Tender