Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የባቲ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
  • Address ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ባቲ ወረዳ: አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0335532123
  • Website
  • Deadline26 Jul 2026, 9:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price399.00
  • Bid Securityለእያንዳንዱ ጨረታ ለምድብ 1 ለተገለጸው ብር 50,000.00 /ሀምሳ ሺህ ብር/፣ ለምድብ 2 ብር 25,000.00፣ ለምድብ 3 6,000.00፣ ለምድብ 4 3,000.00
  • opening date2026-07-26 10:00:00
  • Categories Vehicle tire , Vehicle Spare Parts

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የባቲ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት ለባቲ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ምድብ 1፣ አመታዊ የመኪና መለዋወጫ፣ ምድብ 2 የመኪና ጎማ፣ ምድብ 3 በኪሎ ሜትር የሚቀየሩ የመኪና መለዋወጫ፣ ምድብ 4 አመታዊ የመኪና ጌጣጌጥ እቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የባቲ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የባቲ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት ለባቲ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ምድብ 1፣ አመታዊ የመኪና መለዋወጫ፣ ምድብ 2 የመኪና ጎማ፣ ምድብ 3 በኪሎ ሜትር የሚቀየሩ የመኪና መለዋወጫ፣ ምድብ 4 አመታዊ የመኪና ጌጣጌጥ እቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ።

1.       ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ከሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2.      የገንዘብ መጠኑ ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺ/ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርበታል።

3.      ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በሁለት ቅጂዎች ማለትም ኮፒና ኦርጂናል በማለየት በጥንቃቄ በታሸገ ኤንቨሎፕ ባቲ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በግዥ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።

4.     ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

5.      ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ጨረታ ለምድብ 1 ለተገለጸው ብር 50,000.00 /ሀምሳ ሺህ ብር/፣ ለምድብ 2 ብር 25,000.00፣ ለምድብ 3 6,000.00፣ ለምድብ 4 3,000.00 በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በገቢ መቀቢያ ደረሰኝ በባቲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በምርጫቸው በእንዱ ከዋናው /ኦሪጅናል የመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6.     ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ እና የተጫራቾች መመሪያ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበትን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 15ኛው ቀን በባቲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

7.      ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን ዋናና ቅጂ /Orignal and Copy/ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው ታትሞ ከወጣበት ቀን ከ4/1/2018 ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ማለትም እስከ 19/11/2018 ቀን 3፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በባቲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ማስገባት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት በግልጽ ይከፈታል።

8.     ግዥ ፈጻሚ መ/ቤት ጨረታውን በጥቅል ዋጋ /ሎት/ የሚያወዳድር መሆኑንና ሙሉ የጨረታ ሰነድ ዋጋ ያልሞላ ከጨረታ ውድድር ውጭ የሚሆን መሆኑን እናሳውቃለን።

9.     ተጫራቾት በሰነዱ ላይ ስም፣ ማህተምና ፊርማ አሟልተው መገኘት አለባቸው፤ ስርዝ ድልዝ ካለው ከውድድር ውጪ ይሆናል።

10.    የጨረታ ውጤት ለአሸናፊ ድርጅቶች በአድራሻ ለተሸናፊዎች ደግሞ በግልባጭ በደብዳቤና በጽ/ቤቱ የውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል።

11.     ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

12.    ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ስለጨረታው የበለጠ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ በባቲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ንብረት አስ/ር ቡድን በአካል ቀርበው ወይም በስ.ቁ 0335532123 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ ::

 

ማሳሰቢያ:- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ቦታው ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን አስተዳደር የባቲ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት

Save Tender