Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Commercial Bank of Ethiopia


                                            የሐራጅ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የተበዳሪው ስም የንብረት አስያዥ ስም የመያዣ ንብረቱ መለያ የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር) ሐራጁ የሚከናወንበት ቀን እና ሰዓት
አድራሻ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር/መለያ  የይዞታው

ስፋት

የይዞታው አይነት/የሚሰጠው አገልግሎት
1. አቶ ለገሰ ሙለታ ያሚ እና የሰውዘር አለበል ኃይሉ ተበዳሪዎች ሻሸመኔ ከተማ አለቼ ክ/ከተማ አዋሾ ወረዳ 01 ቀበሌ WBIFBG/A/L/937/09 5000 ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውል ሕንጻ 38,071,965.73 03/11/18 ዓ.ም

3፡00-4፡00 ጠዋት

2. አቶ ማስረሻ ታደሰ ተበዳሪው ፍቼ ከተማ ቡርቃ ጉራ ወረዳ 1356/M-27/2006 400 የንግድ ህንጻ 1,960,015.85 03/11/18 ዓ.ም

4፡00-5፡00 ጠዋት

3. አቶ ተመስገን ጫላ ጃለታ ተበዳሪው ሸገር ከተማ ፉሪ/ክ/ከ የቀድሞ ወረዳ 4 L/349/2003/B6/P1 468 መኖሪያ ቤት 21,582,351.71 03/11/18 ዓ.ም

5፡00-6፡00 ጠዋት

4. ሪሳ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ ተበዳሪው አርሲ ዞን ሳጉሬ ከተማ ቀበሌ 02 5/3066/001/2441/2015 209 የንግድ ቤት 1,814,003.20 03/11/18 ዓ.ም

4፡00-5፡00 ጠዋት

5. ሪሳ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ ነፃነት ናስር አርሲ ዞን አሰላ ከተማ ቀበሌ 10 10651/91/97 200 መኖሪያ ቤት 2,567,870.84 03/11/18 ዓ.ም

4፡00-5፡00 ጠዋት

በመሆኑም፡-

  1. ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ ማቅረብ ተመራጭ ነው፡፡
  2. ከተ.ቁ 1-3 የተዘረዘሩ ንብረቶች ጨረታ የሚከናወነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋናው መስሪያ ቤት 42ኛ (ወለል) ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4203 ሲሆን በተራ ቁጥር 4-5 የተጠቀሱት ንብረቶች ጨረታ የሚከናወነው አሰላ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ነው፡፡
  3. የንግድ ማህበርን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ እና መተዳደርያ ደንብ የያዘና በማህበሩ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል፡፡
  4. ከመኖሪያ ቤት ውጪ ለጨረታ የቀረቡ ንብረቶችን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ሰዉ በሽያጩ ገንዘብ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል፡፡
  5. የጨረታ አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል፡፡
  6. ንብረቶቹን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋ/መስሪያ ቤት 42 ፎቅ በአካል በመቅረብ ባንኩ በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት መጎብኘት ይቻላል፡
  7. በጨረታው ከፍተኛ የሆነ የጨረታ ዋጋ የሰጠ ተጫራች በባንኩ የጨረታ አሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ቀሪ የሽያጩን ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጁ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡
  8. ንብረቶቹን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም፡፡ ገዢው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡
  9. ባንኩ ሐራጁን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

እርማት፡

ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም በታተመው የሪፖርተር ጋዜጣ ላይ በወጣው የሐራጅ ማስታወቂያ በተ.ቀ. 5 ላይ የተገለጸው አቶ ጌቱ ሃይሌ ጨራኮ ለወሰዱት ብድር መከፈል በዋስትናነት የተሰጠው ባለቤትነቱ የአቶ ክፍሌ ዴንቶ የሆነ ንብረት ጨረታ የሚከናወንበት ቀን ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም የሚለዉ ሰኔ 12 ቀን 2018 ተብሎ ይነበብ፡፡ 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111-13-05-08 በመደወል ወይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋና መ/ቤት 42ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ሕግ ክፍል በአካል ቀርቦ ማነጋገር ይቻላል፡፡

 

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

Save Tender