የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ ከታች በሰንጠረዥ የተገለፁትን እቃዎች በጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ ከታች በሰንጠረዥ የተገለፁትን እቃዎች በጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤
|
የሎት ቁጥር
|
የእቃው አይነት
|
|
ሎት- 1
|
የሰራተኛ ሴፍቲ ጫማ እና ኖርማል ጫማ
|
|
ሎት- 2
|
ፎጣ
|
|
ሎት- 3
|
የፅዳት እቃዎች
|
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
1. በኢንዱሰትሪው ሰፕላይ ቼን ማኔጅመንት ቡድን ቢሮ በመምጣት ዝርዝር መረጃ የተጫራቾችን መመሪያ እና የዕቃዎችን ዓይነትና መጠን የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 700 (ሰባት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
2. በዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ ተጫራቹ የዕቃው ዋጋ በሚለው አምድ ስር የሚሸጡበትን የነጠላ ዋጋ በአሃዝ ያለስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኢንቨሎፕ የኢንዱስትሪው ሰፕላይ ቼን ማኔጅመንት ቡድን ቢሮ በተዘጋጅው የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባችሁ።
3. ተጫራቹ የዕቃዎችን የተናጥል ዋጋ ማቅረብ ይኖርበታል።
4. ትክከለኛ የተጫራች ስምና አድራሻ በታሸገው ኢቨሎፕ እና በመጫረቻ ሰነድ ላይ መገለፅ ይኖርበታል።
5. ተጫራቾች የእቃዎችን ለተቀመጠው የነጠላ ዋጋ ድምር የጨረታ መነሻ ዋጋ 2 በመቶ (2%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል። የሚዘጋጀው የጨረታ ማሰከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል።
6. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ዕለት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንዱስትሪው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም
7. ተጫራቾች የጨረታውን ውጤት በኢንዱስትሪው ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከወጣ ቀን ጀምሮ ቅሬታ ካላቸው በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በፁሁፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥራችን 0116 670 485 / 0118 592 286 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ላይ በየገጹ ስምና ፊርማ ማስገባት አለባቸው
10. ተጫራቾች የቫት ሠርተፍኬት፣የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይ ሠርተፍኬት እና ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
11. ኢንዱስትሪው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻችን በመገናኛ ወደ ገርጂ በሚወስደው መንገድ ከአምቼ ዝቅ ብሎ ኒያላ ሞተርስ ፊት ለፊት
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ
