Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Health Bureau (የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ)
  • Address ባህር ዳር ከተማ የአውሮፕላን ማረፊያ መንገድ ከሆምላንድ ሆቴል ፊት ለፊት ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-222-1127
  • Websitehttps://www.arhb.gov.et/
  • Deadline11 May 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-05-11 00:00:00
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የኃይጅንና ሳንቴሽን ሥራዎችን ለማጠናከር የሚያገለግል የቆሻሻ ማስቀመጫ /DUST BIN/ በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

Amhara Health Bureau (የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ)


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የኃይጅንና ሳንቴሽን ሥራዎችን ለማጠናከር የሚያገለግል የቆሻሻ ማስቀመጫ /DUST BIN/ በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ለመወዳደር የተጋበዙ መሆኑን እያሳወቅን፡-

1.     በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።

2.     የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ሰርተፍኬት/ የሚያቀርቡ፡፡

3.     ከላይ በተራ ቁ 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4.     የሚገዛው ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ ከ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር / በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የቫት ሰርተፊኬት ኮፒ ማስያዝ አለበት፡፡

5.     የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የሚያስይዝ፤ ሆኖም የጨረታ ማስከበሪያው ጠቅላላ ዋጋ ከ 500,000.00/አምስት መቶ ሺህ ብር/ መብለጥ የለበትም።

6.     ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት በ15 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

7.     ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን የፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤

8.     ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ16ኛው ቀን 2018 ዓ.ም በ 8:30 ሰዓት ታሽጎ 9፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በተከታዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል፡፡

9.     ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

10. ቢሮው የግዥዉን መጠን እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡

11. የጨረታዉ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሸነፈውን የኃይጅን እና ሳኒቴሽን እቃዎች የጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው ስርጭት /ድልድል/ መሰረት ለጤና ተቋማት ማቅረብ አለበት፡፡

12. በጨረታው የተወዳደረ ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከቢሮው የሰነድ ሽያጭ ክፍል መውሰድ ይችላል፡፡

13. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

14. ስለ ጨረታዉ መረጃ ከፈለጉ አብክመ ጤና ቢሮ ስልክ ቁጥር 058-222-1127 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ

Save Tender