የአርባ ምንጭ ትምህርት ኮሌጅ በ2019 ዓ.ም በጀት ዘመን በግልፅ ጨረታ የተለያዩ ዕቃዎች ግዢ ለመፈፀም ይፈልጋል።
Arba Minch College Of Education (የአርባ ምንጭ ትምህርት ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የአርባ ምንጭ ትምህርት ኮሌጅ በ2019 ዓ.ም በጀት ዘመን በግልፅ ጨረታ የተለያዩ ዕቃዎች ግዢ ለመፈፀም ይፈልጋል። በዚህም መሠረት
| 1. የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፤ | 6. መድሀኒቶችና የህክምና ቁሳቁስ ፤ |
| 2. የጽዳት ዕቃዎች፤ | 7. የፈሳሽ ሳሙና ማምረቻ ከሚካሎች |
| 3. የጽ/መሣሪያ/ስቴሽነሪ ፤ | 8. የስፖርት ዕቃዎች |
| 4. የደንብ ልብስ ፤ | 9. አርት ዕቃዎች |
| 5. የመኪና ጎማ እና የመኪና መለዋወጫ ዕቃ |
ከላይ በተጠቀሰው ዓይነት ንግድ ዘርፍ የተሰማራችሁ ነጋዴዎችና ድርጅቶች የዘመኑን ግብር በመክፈል ፈቃድ ያደሳችሁ፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆናችሁ እንዲሁም የቲን ቁጥር ያላችሁ ነጋዴዎችና ድርጅቶች በማወዳደርና በማጫረት ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከላይ የተገለፀውን መስፈርት የምታሟሉና በተጠቀሰው ዘርፍ የተሰማራችሁ ነጋዴዎችና ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15/ አስራ አምስት / ተከታታይ ቀናት ወደ ኮሌጁ ግዢ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቁጥር 101 ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት በመምጣት ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 አርባምንጭ ትምህርት ኮሌጅ በባንክ ቁጥር 1000021599151 ገቢ በማድረግ መውሰድ ትችላላችሁ።
- በ1ኛ ተራ ቁጥር የተገለፀው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን ጠዋት ከ2 - 4 ሰዓት ናሙናው ታይቶ በናሙና ያለፉ ተወዳዳሪዎች ብቻ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ9:00 ሰዓት ይከፈታል።
- በ2ኛ ተራ ቁጥር የተገለፀው የሚከፈተው በ17ኛው ቀን ጠዋት ከ2 -4 ሰዓት ናሙናው ታይቶ በናሙና ያለፉ ተወዳዳሪዎች ብቻ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ9:00 ሰዓት ይከፈታል።
- በ3ኛ ተራ ቁጥር ላይ የሚገኘው በ18ኛው ቀን ጠዋት ከ2 - 4 ሰዓት ናሙናው ታይቶ በናሙና ያለፉ ተወዳዳሪዎች ብቻ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ9:00 ሰዓት ይከፈታል።
- በ4ኛ ተራ ቁጥር ላይ የሚገኘው በ19ኛው ቀን ጠዋት ከ2 - 4 ሰዓት ናሙናው ታይቶ በናሙና ያለፉ ተወዳዳሪዎች ብቻ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ9:00 ሰዓት ይከፈታል።
- በ5ኛ ተራ ቁጥር የሚገኘው በ20ኛው ቀን ጠዋት ከ2-4 ሰዓት ናሙናው ታይቶ በናሙና ያለፉ ተወዳዳሪዎች ብቻ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ9:00 ሰዓት ይከፈታል።
- በ6ኛ ተራ ቁጥር ላይ የሚገኘው በ21ኛው ቀን ጠዋት ከ2 - 4 ሰዓት ናሙናው ታይቶ በናሙና ያለፉ ተወዳዳሪዎች ብቻ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ9:00 ሰዓት ይከፈታል።
- በ7ኛ ተራ ቁጥር ላይ የሚገኘው በ22ኛው ቀን ጠዋት ከ2 - 4 ሰዓት ናሙናው ታይቶ በናሙና ያለፉ ተወዳዳሪዎች ብቻ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ9:00 ሰዓት ይከፈታል።
- በ8ኛ ተራ ቁጥር ላይ የሚገኘው በ23ኛው ቀን ጠዋት ከ2 - 4 ሰዓት ናሙናው ታይቶ በናሙና ያለፉ ተወዳዳሪዎች ብቻ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ9:00 ሰዓት ይከፈታል።
- በ9ኛ ተራ ቁጥር ላይ የሚገኘው በ24ኛው ቀን ጠዋት ከ2 - 4 ሰዓት ናሙናው ታይቶ በናሙና ያለፉ ተወዳዳሪዎች ብቻ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ9:00 ሰዓት ይከፈታል።
ከላይ የተዘረዘሩት ስምንቱም የዕቃ ዓይነቶች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ዋጋ ፎርሙ ላይ የድርጅቱን ማህተም ስልክና ፊርማ በመሙላትና በመፈረም በፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት አለባችሁ። ተወዳዳሪዎች የጨረታ መክፈቻ ቦታ አርባ ምንጭ ትምህርት ኮሌጅ መሆኑን እየገለፅን ጨረታው የሚከፈተው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ የሚከፈት ይሆናል።
ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ / Bid Bond / በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ Cpo / 10,000 / አሥር ሺህ ብር / ማቅረብ አለባቸው። ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
